ሀላባ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ ገብቷል።
በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሰልጣኝ በሽር አብደላ መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ያደገው እና ከወጣቱ አሰልጣኝ ጋር በፕሪምየር ሊጉም ላይ የምንመለከታቸው ሀላባ ከተማ ወደ ዝውውሩ በመግባት በይፋ ሁለት የውጪ ተጫዋቾች በማስፈረም ዝውውሩን መቀላቀላቸውን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።
የመጀመሪያው ፈራሚ ጋናዊው ተከላካይ ካሌብ አማንኩዋ ሆኗል። ከሦስት አመት በፊት የሀገሩን ክለብ ህርትስ ኦፎክን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለፉትን ሦስት አመታት ቆይታን ማድረግ የቻለ ሲሆን ከክለቡም ጋር የ2016 የሊጉን ዋንጫ ማሳካት የቻለ ሲሆን ቀጣዩ መዳረሻው አዲስ አዳጊው ሀላባ ሆኗል።
ሌላኛው አጥቂው ኮንኮኒ ሀፊዝ ማረፊያው ሀላባ ከተማ ሆኗል። የታንዛኒያውን ሀያል ክለብ ያንጋ አፍሪካን ከለቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ ቡና መለያ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ጋር የተዋወቀው ግዙፉ አጥቂ ከወልዋሎ ጋር የተጠናቀቀውን አመት የኢትዮጵያ ዋንጫን ካሳካ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው በርበሬዎቹ ሆነዋል።
አስተያየት ይስጡ