ከአምስት አመታት በኋላ ከወላይታ ድቻ ጋር የተለያየው የግብ ዘብ ወደ ፈረሰኞቹ አመራ።
ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ላለፉት አምስት አመታት ክለቡን ሲያገለግል የቆየው እና የአንድ አመት ቀሪ ውለሸ እየቀረው በትላንትናው ዕለት በይፋ የተለያየው ግብ ጠባቂው ቢኒያም ገነቱ ቀጣይ ማረፊያው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለመሆን ተቃርቧል።
ከሌላኛውን የግብ ዘብ ሰይድ ሀብታሙ ጋር ያልተስማማው ቅዱስ ጊዮርጊስ በዛሬው ዕለት ሁሉንም አዳዲስ ተጫዋቾች የሜዲካል ምርመራ እንደሚያደርግ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ