የሀዋሳው ኮረም ሜዳ ፍሬ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ አመራ።

ከሀዋሳ ኮረም ሜዳ ላይ መነሻውን ካደረገ በኋላ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ወጣት ቡድን አገልገልሎ ላለፉት ሁለት አመታት ደግሞ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ዋናው ቡድን በፕሪምየር ሊጉ አስደናቂ አቋሙን ሲያሳየን የነበረው የመሐል ተከላካዩ ቢኒያም በቀለ ትላንት ከኤሌክትሪክ ጋር የነበረው ድርድር ሳይሳካ ቀርቶ በመጨረሻም በሁለት አመት ውል አዲሱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች መሆኑ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ