ባህርዳር ከተማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አግኝቷል።
ከአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ጋር በቀጣዩም የውድድር ዘመን የምንመለከተው ባህርዳር ከተማ የመጀመሪያው ፈራሚውን አግኝቷል።

ባህርዳር ከተማን የተቀላቀለው ቀዳሚው ተጫዋች የግራ መስመር የግራ መስመር ተከላካዩ ዮዳሄ ዳዊት ሆኗል። ከመቻል ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ላለፉት አራት አመታት በዋናው ቡድን ቆይታ ያደረገው ከትልውድ ሀገሩ ሀዋሳ የተገኘው ተጫዋቹ የጣናውን ሞገድ መቀላቀሉ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ