ከማዕዘን ምት አስደናቂ ጎል ያስቆጠረው ተጫዋች ቅዱስ ጊዮርጊስን ተቀላቀለ።
በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከታዩ ምርጥ የግራ መስመር ተከላካዮች መካከል አንዱ መሆን የቻለው ኢትዮ ኤሌክትሪክን ከታችኛው የሊግ ዕርከን ጀምሮ በፕሪምየር ሊጉ ለተከታታይ ሁለት አመታት ሲያገለግል የቆየው የግራ መስመር ተከላካዩ ያሬድ የማነ ትላንት ምሽት በይፋ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዋች ሆኗል።

ባለፈው የ2017 የውድድር ዘመን ምድረገነት ሽረ ላይ ከማዕዘን ምት ኢትዮ ኤሌክትሪክ 1ለ0 ሲያሸንፍ ባስቆጠራት አስደናቂ ጎል ብዙዎች ያስታውሱታል።
አስተያየት ይስጡ