ፊፋ በካሜሮናዊው አጥቂ ክስ መቐለን አገደ።
በ2017 የውድድር ዘመን መቐለ 70 እንደርታን ከተቀላቀሉ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች መካከል ካሜሮናዊው አጥቂ ማንይክሬ ዳንጉሞ አንዱ ነው። የሳይፕረሱን ክለብ የንካሚ ኤኬን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ሞዓም አናብስቱን የተቀላቀለው ይህ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ በክለቡ ቆይታ ማድረግ የቻለ ሲሆን ብዙም አመርቂ ጊዜን በክለቡ ማሳለፍ ባይችልም ክለቡ ያልከፈለኝ ደመወዝ አለ ብሎ ለፊፋ በማመልከቱ ክለቡ ለተጫዋቾቹ እስከሚከፈል ድረስ መታገዱን ያገኘሁት መረጃ ይጠቁማል።

በያዝነው አመት መቐለ 70 እንደርታ ከፕሪምየር ሊጉ መውረዱም ይታወሳል።
አስተያየት ይስጡ