ሸገር ከተማን በጊዜያዊ እና ዋና ሚና እየመሩ አመቱን የቋጩት አሰልጣኝ ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ከስምምነት ደርሰዋል።

በ2018 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ለመጀመሪያ ጊዜ በማደግ የተካፈለው ሸገር ከተማ አመቱን በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ቢጀምርም አሰልጣኙን ከውጤት መጥፋት ጋር በተገናኘ በማሰናበት ረዳት አሰልጣኝ የነበሩትን ዶ/ር እያሱ መርሀፅድቅን በጊዜያዊ እና በመጨረሻም በዋና አሰልጣኝነት ሚና በመሾም አመቱን አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ እንዲያጠናቅቅ አድርገዋል። የቀድሞው የሀሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህር ፣ የድሬዳዋ ከተማ የቴክኒክ ዳይሬክተር እንዲሁም በሀድያ ሆሳዕና ጅማ አባጅፋር እና ፋሲል ከነማ በረዳት አሰልጣኝነት ያገለገሉት አሰልጣኝ ያስመዘገቡት ውጤት አመርቂ መሆኑን ተከትሎ ሌሎች ጉዳዮችም ተካተው አሰልጣኙ በክለቡ የቀጣይ አመት በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ ክለቡ ከአሰልጣኙ ጋር መስማማታቸውን ሀትሪክ ስፖርት ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ