ፈረሰኞቹ ሦስተኛው ፈራሚ የግራ መስመር ተከላካዩ ሆኗል።
ሰርቪያዊውን አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊት ሚቾን በዋና አሰልጣኝነት እንደሚሾም የሚጠበቀው ቅዱስ ጊዮርጊስ የግራ መስመር ተከላካዩ አብዱሰላም የሱፍን ሦስተኛ ፈራሚው አድርጓል።

የቀድሞው የደሴ ከተማ እና ሀምበሪቾ ዱራሜ ተጫዋች በድሬዳዋ ከተማ ላለፉት ሁለት አመታት ቆይታን ካደረገ በኋላ ከአማካዩ ብሩክ እንዳለ እና ከመስመር አጥቂው ተመስገን ብርሀኑ በመቀጠል የፈረሰኞቹ ሦስተኛው ፈራሚ መሆን ችሏል።
የተጫዋቹ ዝውውር ነገ ረፋድ ይፋ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ