ወላይታ ድቻ አንድ ተጫዋች ሲያስፈርም የነባር ተጫዋቹን ውልን አድሷል!
የአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪን ኮንትራት ትላንት በሁለት አመት ውል ያራዘመው ወላይታ ድቻ ዛሬ አንድ አዲስ ተጫዋች ሲያስፈርም የመሐል ተከላካዩን ውል ደግሞ አድሷል።

የቀድሞው የሺንሺቶ ከተማ ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባለፈው አመት በአርባምንጭ ከተማ አመቱን ያሳለፈው የግራ መስመር ተከላካዩ ኤፍሬም ታምራት ወላይታ ድቻን በይፋ ሲቀላቀል ፣ በ2009 ከወላይታ ድቻ ወጣት ቡድን አድጎ በኋላም ለዋናው ቡድን እንዲሁም ደግሞ በከፍተኛ ሊጎቹ ሶዶ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ የተጫወተው የመሐል ተከላካዩ ውብሸት ክፍሌ በክለቡ ለተጨማሪ አመት ውሉን አራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ