የጦና ንቦቹን በሊጉ ማቆየት የቻሉት አሰልጣኝ በሁለት አመት ውላቸውን አራዝመዋል።
ወላይታ ድቻን ከታችኛው የሊግ ዕርከን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካሳደግ በኋላ በ2010 የውድድር ዘመን ተለያይቶ የነበረው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ከአርባምንጭ ከተማ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዳት እና ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ከሰራ ከረጅም አመታት በኋላ ወደ ቀደመ ክለቡ በመመለስ ወላይታ ድቻን በያዝነው አጋማሽ በመረከብ ክለቡ ከነበረበት ወራጅ ቦታ በተሻለ ሆኖ መቋጨት እንዲችል አድርገዋል።

በዛሬው ዕለት የክለቡ ቦርድ ክለቡን ከገመገመ በኋላ አሰልጣኙ ያመጡትን አመርቂ ውጤት በማወደስ ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት ክለቡን እያሰለጠ እንዲቆይ ውሉን በይፋ ማራዘሙን ክለቡ ያደረሰን መረጃ ይጠቁማል።
አስተያየት ይስጡ