መነሻ ገጽ ዜናዎች ሦስት ተጫዋቾች ለሙከራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን አምርተዋል
ዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሦስት ተጫዋቾች ለሙከራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን አምርተዋል

አጋራ
አጋራ

ሦስት ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾች ለሙከራ ዛሬ ረፋድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ማምራታቸውን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጣለች።

ከሰሞኑ የኢትዮጵያ መድን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ ለሙከራ ወደ ደቡብ አፍሪካ በማምራት ስቴለን ቦሴች በተባለው የሀገሪቱ የፕሪምየር ሊግ ተካፋዩ ክለብ የሙከራ ጊዜውን እያሳለፈ እንደሚገኝ ከቀናት በፊት በዘገባዬ ማሳወቄ ይታወሳል። አዲስ አሰልጣኝ ከሰሞኑ የቀጠረው ምስረታው ካደረገም ዘጠኝ አመት ብቻ ያስቆጠረው ስቴለን ቦሴች ከአቡበከር ኑራ በተጨማሪ ሦስት ኢትዮጵያዊያን ተጫዋቾችን ማለትም አማኑኤል ተርፉ ፣ መሐመድ ኑርናስር እና አብዱሰላም የሱፍን የሙከራ ጥሪን አቅርቦላቸው ተጫዋቾቹ ዛሬ ዕሁድ ረፋድ በራሳቸው ትኬት በመቁረጥ ወደ ስፍራው እንደተጓዙ ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ ችላለች።

የቀድሞው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና በኢራቁ አል ናፍጥር ባስራ ክለብ እየተጫወተ የቆየው ተከላካዩ አማኑኤል ተርፉ ፣ በጅማ አባጅፋር ፣ ኢትዮጵያ ቡና እና በድሬዳዋ ከተማ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት ያሳለፈው አጥቂው መሐመድ ኑርናስር እና የቀድሞው የደሴ ከተማ ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ እንዲሁም ላለፉት ሁለት የውድድር ዘመናት በድሬዳዋ ከተማ መለያ ቆይታን ማድረግ የቻለው የግራ መስመር ተከላካዩ አብዱሰላም የሱፍ ለሳምንታት ሙከራ ሦስቱም ዛሬ ወደ ስፍራው ተጉዘዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...