የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በቀጣዩ አመት የ2019 በ18 ክለቦች መካከል ለሚደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ከአሁኑ በየሀገሩ የሚገኙ ሜዳዎችን በመዟዟር እየተመለከተ ይገኛል።

የባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም በከተማዋ ያሉ የልምምድ ሜዳዎች እና ሆቴሎች የፋሲል ከነማው ጎንደር አፄ ፋሲለ ደስ ስታዲየም የልምምድ ሜዳዎቿ እና ሆቴሎቿ የጋሞ ጨንቻ መወዳደሪያ ተብሎ የተመዘገበው የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም በከተማዋ የሚገኙ የልምምድ ሜዳዎች እና ሆቴሎች እንዲሁም ደግሞ ትላንት ወላይታ ድቻ እና ሀላባ ከተማ በጋራ የሚጠቀሙት የሀላባ አዲሱ ስታዲየም በከተማዋ የሚገኙ የልምምድ ሜዳዎች እና ሆቴሎችን እስከ አሁን የተመለከቱ ሲሆን ዛሬ ደግሞ የአክሲዮን ማህበሩ አባላት በዶ/ር ወገኔ ዋልተንጉስ ፣ አቶ አሰፋ ሆሲሶ እና አቶ ልዑል ሐይሌ እየተመራ የሀድያ ሆሳዕናውን ዕድሳት የተደረገለትን የአቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ፣ በከተማዋ የሚገኙ የልምምድ ሜዳዎች እና ሆቴሎችን መመልከት ችለዋል። በነገው ዕለት የተላከው የአክሲዮን ማህበሩ አባላት የሲዳማ ቡና እና የሀዋሳ ከነማን የመጫወቻ ሜዳ የሆነውን የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም በከተማዋ የሚገኙ የልምምድ ሜዳዎች እና ሆቴሎችን ከተመለከተ በኋላ በቀጣይ ወደ አዳማ ከተማ ፣ አዲስ አበባ እንዲሁም መሰል ከተሞች በመሔድ ግምገማው የሚቀጥል ሲሆን በግምገማው መሟላት አለባቸው የተባሉ መመሪያዎች ከተሰጡ በኋላ ውድድር ማካሄድ ይችላሉ የሚሉትን ዝርዝር ውሳኔዎች እስከ ሐምሌ መጨረሻ የሚያሳውቁ ይሆናል።


አስተያየት ይስጡ