ሀገራችንን ወክሎ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ የሚካፈለው ሲዳማ ቡና የቅድመ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታውን መቼ እንደሚያደርግ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን መሆኑን ያረጋገጠው ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ መርሀግብር ላይ ይወክላል። የሊጉን ዋንጫ በማንሳቱ በመድረኩ የሚካፈለው ክለቡ በቀጣዩ የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታዎቹን መቼ እንደሚያደርግ ለማወቅ ችለናል።
በዚህም መሠረት የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከነሀሴ 29 እስከ ጳጉሜ 1/2018 የመልስ ጨዋታዎችን ደግሞ ከመስከረም 1 እስከ 3/2019 ባሉ ቀናት መካከል እንደሚያደርግ ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ