መነሻ ገጽ ኢትዮጵያ መድህን አቡበከር ኑራ ነገ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራል
ኢትዮጵያ መድህንዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

አቡበከር ኑራ ነገ ጠዋት ወደ ደቡብ አፍሪካ ያመራል

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑራ በደቡብ አፍሪካ ፕሪምየር ሊግ ዘንድሮ ዘጠነኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው ከተመሠረተም ዘጠኝ አመት በሞላው ክለብ ሙከራን ለማድረግ ነገ ረፋድ ወደ ኬፕ ታውን ይጓዛል።

ከመቱ ከተማ ከተገኘ በኋላ በወሎ ኮምቦልቻ ፣ ጅማ አባጅፋር ፣ ሰበታ ከተማ እና ባህርዳር ከተማ እንዲሁም ላለፉት አራት አመታት ደግሞ የኢትዮጵያ መድን ግብ ጠባቂ በመሆን አስደናቂ ብቃቱን ከማሳየቱ ባለፈ ከክለቡ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ያነሳው የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራ ከወራት በፊት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሙከራ ሊያመራ እንደሆነ የጠቆምን ሲሆን ነገ የሚጓዝበትን ክለብ ሀትሪክ ስፖርት ማረጋገጥ ችላለች።

ከወራቶች በፊት ኢትዮጵያ ግብፅን በማጣሪያ ጨዋታ ገጥማ አስደናቂ አቋሙን በማሳየቱ በበርካቶች አይን ውስጥ ገብቶ የነበረው ቁመታሙ የግብ ዘብ ያንን መነሻ በማድረግ ከተመሠረተ ዘጠኝ አመት የሞላው እና ዘንድሮ ደግሞ በደቡብ አፍሪካ ፕሪምየር ሊግ ዘጠነኛ ሆኖ ማጠናቀቅ በቻለው ስቴል ቦሴች ክለብ የሙከራ ዕድልን አግኝቶ ነገ ጠዋት ሦስት ሰአት ወደ ስፍራው እንደሚያመራ ለዝግጅት ክፍላችን ጠቁሟል።

በያዝነው ወር መጨረሻ ከመድን ጋር ኮንትራቱ የሚያበቃው ግብ ጠባቂው በኬፕ ታውኑ ክለብ ውስጥ ለሳምንታት የሙከራ ጊዜ እንደሚኖረውም ጭምር ሰምተናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...