ኢትዮጵያዊውን አማካይ በቀጣይ እናስተዋውቃችሁ።

ትውልዱ በመዲናችን አዲስ አበባ ከኢትዮጵያዊያን ወላጆች ቢሆንም እግር ኳስን በደንብ መጫወት የጀመረው ግን ወደ ኖርዌይ ካመራ በኋላ እንደሆነ ይናገራል በአማካይ ቦታ ላይ የሚጫወተው የ28 አመቱ ተጫዋች ሆሬኑስ ዘውዱ ታደሠ።
አንድ ሜትር ከሰባ አምስት ሴንቲ ሜትር ቁመት ባለቤቱ ተጫዋች በኖርዌዩ ቨርዳን የስልጠና ማዕከል ውስጥ እግር ኳስን ከጀመረ በኋላ በመቀጠል ደግሞ ሊቫንገር ፣ ክርስቴን ሱንድ ቢኬ እና ሳንድስ ሁልፍ በተባሉ የሀገሪቱ የተለያዩ ክለቦች ቆይታን ካደረገ በኋላ በአሁኑ ሰዓት ኦቮስ ሊጋ እየተባለ በሚጠራው ሁለተኛው የኖርዌይ ሊግ ተካፋዩ ኢገር ሱንድስ ኤኬ በመጫወት ላይ የሚገኝ ሲሆን ኢትዮጵያ ወክሎ ደግሞ መለያዋን መልበስ እንደሚፈልግ ደጋግሞ ሲናገርም ተጠምዷል።
አስተያየት ይስጡ