በኮንፍረንስ ሊግ ቼልሲ ላይ ጎል ያስቆጠረው የአሁኑ የQPR ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ማነው ?

አባቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን እናቱ ደግሞ የኤልሳቫዶር ዜግነት አላት እርሱ የተወለደው ደግሞ በሲውዲኗ ሁሜያ በምትባል ቦታ ሲሆን እግር ኳስን የጀመረው ገና የአስር አመት ልጅ እያለ ነበርም ፣ በአሁኑ ሰዓት 19 አመቱ ላይ የሚገኘው በሙሉ መጠሪያ ስሙ አይዛክ አሌክስአንደር አለማየሁ ሙሉጌታ ወይም በአጭሩ በእግር ኳስ መጠሪያው አይዛክ አለማየሁ ፣ በቤተሰቦቹ በደንብ እየተደገፈ እግር ኳስን በሲውዲኑ ዲጁር ጋርደንስ አካዳሚ ጀምሮ በኋላም ከፍ እያለ ሲመጣ በስዊዲን ፕሪምየር ሊግ ለሚካፈለው ለዋናው አሳዳጊ ክለቡ በፕሪምየር ሊግ ጭምር በሁለት አጋጣሚዎች ማገልገል የቻለ ሲሆን በተለይ ደግሞ በ2025 በአውሮፓ ኮንፍረንስ ሊግ ዲጁር ጋርደን በሜዳው በወቅቱ አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካው ቼልሲ እየተመራ 4ለ1 በሆነ ውጤት ሽንፈትን ሲያስተናግድ ብቸኛዋን ጎል ለሲውዲኑ ክለብ ማስቆጠር የቻለው ይህው ኢትዮጵያዊ ደም ያለው አይዛክ አለማየሁ ነበር።

ለሌላኛው የሲውዲኑ ክለብ ኤፍ ሲ ስቶክ ሆልም እንዲሁም ወደ ሆላንድ በማምራት ለፌኖርድ ግልጋሎት መስጠት የቻለው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ባለፈው የክረምት ዝውውር ወደ እንግሊዝ በመምጣት ለQueens Park Rangers (QPR) በመቀላቀል እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን በቀጣዩ አመት በቻምፒየን ሺፑ ክለብ እንደምንመለከተው በሚጠበቀው ከ21 አመት በታች ቡድኑ ውስጥም በመጫወት ላይ ይገኛል።

ለሲውዲን ከ17 ፣ ከ19 እና ከ21 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች በማጣሪያ እና በአውሮፓ ዋንጫ ተሰልፎ መጫወት የቻለው ተጫዋቹ በቅርቡ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ከአባቱ ጋር መጥቶ ሀገራችንን መጎብኘት የቻለ ሲሆን የሀገሪቱን መለያ እንዲለብስም አባቱ ጥረት እንደሚያደርጉም ጠቁመዋል።

አስተያየት ይስጡ