በጀርመን የሚገኘው የመስመር ተከላካይ ማነው ?

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ነው የተገኘው በጀርመኗ ፍራንክፈርት ከተማ ደግሞ ተወልዶ አድጓል ወጣቱ የቀኝ መስመር ተከላካይ ናትናኤል አብርሀ። እግር ኳስን ገና በጨቅላ ዕድሜው ጊቢው ውስጥ የጀመረው ይህ የ18 አመት ወጣት ተጫዋች በቤተሰቦቹ ብርቱ ዕገዛ ማካቢ ፍራንክፈርት በሚባል አካዳሚ ተነስቶ ብላው ገሉ ፍራንክፈርት እስከ ተባለ ሌላ አካዳሚም የልጅነት ስልጠናውን በአግባቡ በመውሰድ ራሱን በደንብ ማጎልበትምፈ ችሏል።

በመቀጠል ወደ ታላቁ የጀርመን ወጣት አካዳሚ ወደ ሆነው የፍራክፈር ከ17 አመት በታች ቡድን በማቅናት ከተጫወተ በኋላ ወደ ሆፈንየም ከ19 አመት በታች ቡድን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ወደ ሆፈንየም ዋናው ቡድን ለማደግ በሚያንደረድረው ሁለተኛው የሆፈንየም ቡድን ውስጥ ጥሩ አቅሙን እያሳየ ይገኛል። ለቤተሰቦቹ የትውልድ ሀገር ኢትዮጵያ የመጫወት ህልም እንዳለው የሚገልፀው እና ለጀርመን ከ16 ፣ 17 ፣ 18 እና 19 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ በመጫወት ጥሩ ግልጋሎትም ሰጥቷል።
አስተያየት ይስጡ