በስፔኑ ላስፓልማስ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ።

መጠሪያ ስሙ ኦስካር ሽመልስ ጊል ሊዊስ ይባላል ትውልዱ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ቢላ ወረዳ ውስጥ ነው። ከኢትዮጵያውያን ቤተሰብ የተገኘው እና እግር ኳስን ለማደጎ ባቀናባት ስፔን ውስጥ መጀመር የቻለው ይህ ወጣት የ19 አመት የመሐል ተከላካይ በስፔኑ ቪያሪያል ወጣት ቡድን መነሻው ሲሆን በመቀጠልም በሁለት አጋጣሚዎች ለሲዲ ሎድ እና ቪያሪያል የልጅነት ህልሙን ለማሳካት በስልጠና ከቆየ በኋላ ወደ ስፔን ላሊጋው ከፍ ብሎ ለመገኘትም በአሁኑ ሰዓት በላስ ፓልማስ ከ19 አመት በታች ቡድን ውስጥ ቆይታን በማድረግ ላይ ይገኛል።

ለስፔን ከ15 አመት በታች ጀምሮ በ16 እና ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች ውስጥ ጭምር ለመጠራት የበቃው ይህ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ኢትዮጵያ መጫወት እንደሚፈልግ ከስፔን አንድ ሚዲያ ጋር መጫወት እንደሚፈልግም ተናግሯል።
አስተያየት ይስጡ