መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንጋፋው አሰልጣኝ ወደ አሰልጣኝነት ይመለሱ ይሆን ?
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አንጋፋው አሰልጣኝ ወደ አሰልጣኝነት ይመለሱ ይሆን ?

አጋራ
አጋራ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ለቀድሞው ተጫዋቹ እና አሰልጣኙ አዲስ ሚናን ለመስጠት ከጫፍ ደርሷል።

የተጫዋችነት ጊዜያቸውን ካገባደዱ በኋላ የስልጠናውን አለም በ1980ዎቹ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን መጀመር የቻሉት አንጋፋው አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ማንሳት የቻሉ ሲሆን በየመን ክለቦችም የተሳኩ አመታትን አሳልፈዋል። በሀገራችን ክለቦች በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ሰበታ ከተማ ፣ መቻል ፣ ፋሲል ከነማ ፣ ሲዳማ ቡና እና እንዲሁም በ1997 ወዳሰለጠኑት አዳማ ከተማ በያዝነዝ አመት አምርተው የነበሩት አሰልጣኙ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ጋር የጥሎ ማለፍ ዋንጫን ደግሞ ከመቻል ጋር ማንሳትም ችለዋል።

በያዝነው የውድድር ዘመን በአዳማ ከተማ ጅምራቸውን ቢያደርጉም በሂደት ከክለቡ መለያየት የቻሉት አሰልጣኙ የቀድሞው ክለባቸው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከገባት ፈተና ለማላቀቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ካደረጉት መካከል አንዱ መሆን የቻሉ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ክለቡ አዲስ ሹመት ሊሰጣቸው በዝግጅት ላይ እንዳለ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።

በአሁኑ ሰዓት የቅዱስ ጊዮርጊስ ጊዜያዊ የቦርድ አባል ሆነው እስከ ጥቅምት ወር ድረስ የተመረጡት አሰልጣኝ ስዩም ከበደ በቀጣይ ወደ አሰልጣኝነት ህይወታቸውን ይመለሳሉ ወይስ በተሰጣቸው ሚና ይቀጥላል የሚለው ጉዳይ በርካቶችን እያነጋገረ የሚገኝ ሲሆን እኔም ለአሰልጣኙ ጥያቄ አቅርቤላቸው በቅዱስ ጊዮርጊስ የተሰጣቸው የቦርድ አባልነት ጊዜያዊ በመሆኑ ከጥቅምት ወር በኋላ ክለብ ካገኙ ማሰልጠን እንደሚችል ነግረውኝ ነገር ግን አሰልጣኙ በግልፅ ባይነግሩኝም በፈረሰኞቹ ቤት አዲስ ሚና ሊሰጣቸውም በዕቅድ መያዙን ነግረውኛል ባደረኩት ማጣራት ግን አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ቀጣዩ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቴክኒክ ዳይሬክተር የመሆን ዕድላቸው የሰፋ መሆኑን ለማወቅ ችያለሁ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...