መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የፈረሰኞቹ ዕግድ አሁንም አልተነሳም
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የፈረሰኞቹ ዕግድ አሁንም አልተነሳም

አጋራ
አጋራ

በፊፋ በተጫዋቾቹ ክስ ቀርቦበት የነበረው እና ለጉዳዩ ዕልባት መስጠት የቻለው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕግዱ ግን ፀንቶበታል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በ2017 ዓ.ም. የውድድር ዘመን ላስፈረማቸው አራት የውጪ ተጫዋቾች ደመወዝ መክፈል ባለመቻሉ ምክንያት ተጫዋቾቹ ለፊፋ ክስ በማቅረባቸው ለሁለት የዝውውር ወቅቶች ክለቡ ተጫዋቾችን እንዳያስፈርም ዕገዳ መጣሉ ይታወሳል ። ይህንንም ተከትሎ በተሰጠው 30 ቀን ውስጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ መክፈል ባለመቻሉና ይግባኝም ባለመጠየቁ ዕገዳው የፀና ሆኖበታል፡፡

ክለቡ ከአቶ ጀማል አህመድ ከሚድሮክ ስራ አስፈፃሚ በስጦታ ያገኘውን ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ለአራቱም ተጫዋቾች ከእነ ቅጣቱ የከፈለ ሲሆን ቅጣቱም ሙሉ በሙሉ እንደሚነሳለትም በሁሉም የስፖርት ቤተሰብ እና የእግር ኳስ አመራር ዘንድ እምነት ነበር፡፡ የቅጣት ክፍያውን ከእነ ወለዱ ሲከፍልም ፊፋ በእያንዳንዱ አራት ተጫዋቾች ተቀጥቶ የነበረው የዝውውር ዕገዳ እንደተነሳም የሚገልፁ አራት ደብዳቤዎችን ፈረሰኞቹ ከፊፋ ተቀብለዋል። ክፍያው በመፈፀሙ ክለቡ ይጠብቀው የነበረውን የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ፣ ከሊጉ በቅጣት የመውረድ ስጋት ከመዳኑም በላይ በሚመጣው የዝውውር መስኮት የሀገር ውስጥ ተጫዋቾችን ማስፈረም እንዲችል አድርጎታል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የውድድር ዘመኑን የተሻለ ደረጃ ይዞ ለማጠናቀቅ አራት የውጪ ሀገር ተጫዋቾችን ለማስፈረም ወደ ሀገር ውስጥ ሲያስመጣ እዚህ መጥተው መፈረም የሚችሉ መሆኑን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማረጋገጫ በማግኘቱ ነበር፡፡ ነገር ግን ተጫዋቾቹ የህክምና ምርመራ አጠናቅቀው በክለባችን ቲኤምኤስ ለመመዝገብ ሲሞከሩ ክለቡ ዕገዳው እንዳልተነሳለት ታውቋል፡፡

ጉዳዩንም በመያዝ ወደ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ብናመራም ፌዴሬሽኑና ክለቡ ጋር ያለው መረጃ ተመሳሳይ መሆኑን በመሆኑ በአራቱ ተጫዋቾች ክስ የተጣለበትን ቅጣት ሙሉ በሙሉ ከፍሎ መጨረሱን የሚገልፅ ደብዳቤ ማግኘቱንና ዕግዱ ግን አለመነሳቱን ክለቡ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የተጫዋቾቹ ጠበቃ ጭምር ቢፅፉም በተደጋጋሚ ከፊፋ የተገኘው ህዳር 11 ቀን 2018 ዓ.ም በFPSD-20952 መዝገብ ቁጥር በተሰጠው ውሳኔ የፀና መሆኑን የሚገልፅ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መልዕክቶችን ነበር፡፡

በመሆኑም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አሜሪካ ማያሚ እና ሲዊዘርላንድ ዙሪክ ከተሞች በመገኘት የዚህን ውሳኔ ማብራሪያ የሚጠይቁ ሁለት የፊፋ ፈቃድና ልምድ ያላቸውን ጠበቆች በመቅጠር ጉዳዩ በክለባችን አሸናፊነት እንዲቋጭ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅሟል። ሆኖም ፊፋ በፊፋ የተጫዋቾች ሁኔታና ዝውውር ደንብ (RSTP) አንቀጽ 17 ንዑስ አንቀጽ 4 መሰረት ቀሪው የምዝገባ ዕገዳ ሙሉ በሙሉ ሊጠናቀቅ እንደሚገባ ነገር ግን ክለባችን የሀገር ውስጥ ተጫዋቾችን ብቻ ማስፈረም እንደሚችል አቋሙን አጽንቷል።

በዚህም መሰረት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ፊፋ የጣለበትን የሁለት የተጫዋቾች ዝውውር ዕገዳ ለማሟላት በቀጣይ በሚከፈተው የክረምት የዝውውር መስኮት ብቻ የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው ተጫዋቾችን ከማስፈረም የሚታገድ ይሆናል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...