መነሻ ገጽ ዜናዎች ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ፈረሰኞቹ እና ቡናማዎቹም አሸንፈዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ፈረሰኞቹ እና ቡናማዎቹም አሸንፈዋል

አጋራ
አጋራ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡናም በደጋፊያቸው ፊት በደስታ ሲቋጩ የድቻ እና ንግድ ባንክ ጨዋታ ደግሞ 0ለ0 አልቋል።

ከሰሞኑ ከነበረበት ችግር እፎይታን ያገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በበርካታ ደጋፊዎቹ ፊት ወሳኝ ድልን ከስምንት ድል አልባ ጉዞ በኋላ ሀድያ ሆሳዕናን 2ለ1 በመርታት አስመዝግቧል። በተለየ ተነሳሽነት ሜዳ ላይ ሲደምቁ የታዩት ፈረሰኞቹ 43ኛው ደቂቃ በጥሩ የእግር ስራ ሳጥን ውስጥ በፈጠሩት ቅብብል የአብስራ ጎሳዬ ከሀብታሙ ጉልላት የደረሰውን ኳስ ጎል በማድረግ ቡድኑን ቀዳሚ አድርጓል።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታው ላይ መጠነኛ መሻሻል ለማሳየት የሞከሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች 63ኛው ደቂቃ ላይ በፈጣን እንቅስቃሴ ተመስገን ብርሀኑ ከግራ ወደ ውስጥ ሲያሻማ ለቅዱስ ጊዮርጊስ የመሪነት ጎል ያስቆጠረው የአብስራ ጎሳዬ በራሱ መረብ ላይ ለተጋጣሚ ቡድን ጎል በማከል ጨዋታው ወደ 1ለ1 ተሸጋግሯል። ጨዋታው በዚህ ውጤት የሚጠናቀቅ ቢመስልም አሸንፎ ለመውጣት በብርቱ ጥረት ማድረግ የቻሉት ፈረሰኞቹ በጭማሪው ደቂቃ ላይ በቀድሞው የወልቂጤ ተጫዋች ፉዓድ አብደላ 90+3 ላይ የግል ጥረቱን ተጠቅሞ ባስቆጠራት ጎል ለቅዱስ ጊዮርጊስ ጣፋጭን ድል ያስገኘች ጎል ማስቆጠር ችሎ ጨዋታው ተቋጭቷል።

ሁለቱን የመዲናይቱን ክለቦች ባገናኘው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በድል አጠናቋል። ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር የተሻለ አቀራረብ በነበረው እና ተመጣጣኝ ፉክክርን ከጎል ሙከራ ጋር ባስተዋልበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና አሸናፊ ሆኗል። 47ኛው ደቂቃ ላይ ኤርሚያስ ሹምበዛ መሬት ለመሬት አሾልኮ የሰጠውን ኳስ ቢኒያም ጌታቸው በግምት ከ25 ሜትር ርቀት የአቡበከር ነለራ መረብ ላይ አስደናቂ ጎል አስቆጥሮ የቡናማዎቹን ደጋፊዎች በደስታ አፍክቶ ጨዋታው ፍፃሜውን 1ለ0 በሆነ ውጤት አግኝቷል።

ወላይታ ድቻን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባናኘው እና ጠንካራ ፉክክር ያስመለከተን ጨዋታ ጥሩ በሆኑ የሜዳ ላይ እንቅስቃሴዎች ደምቆ በተለይ ወላይታ ድቻዎች በሽግግር ንግድ ባንኮች ኳስን በመቆጣጠር በይበልጥ መንቀሳቀስን መርጠው ቢታዩም በከባድ ዝናብ የታጀበው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ያለ ጎል ተጠናቋል።

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ከተከታዩ ሀዋሳ በስምንት ያሰፋበትን ወሳኝ ድል በመቐለ 70 እንደርታ ላይ ተጎናፅፏል። ኢንተርናሽናል ዳኛ ባህሩ ተካ በብቃት መርተው ባጠናቀቁት ጨዋታ በማጥቃት ደመ ነብስ የተዋጣላቸው ሲዳማ ቡናዎች በመጀመሪያው አጋማሽ እንደነበራቸው የበላይነት ጎል ያስቆጠሩት 25ኛው ደቂቃ ላይ ነበር። በጨዋታው ልዩነት መፍጠር የቻሉት አቤል ያለው እና ፍቅረየሱስ ተወልደብርሃን በፈጠሩት አስደናቂ አንድ ሁለት ፍቅረየሱስ አሾልኮ ሲሰጠው አቤል ያለው ሶፎኒያስ ሰይፈ መረብ በማሳረፍ በዝናብ ቡድኑን ለሚደግፈው ደጋፊ ጮቤ አስረግጧል።

ጨዋታው ከዕረፍት ሲመለስ በተለይ የተጫዋች አጠቃቀም በማስተካከል በቅያሪ ተጫዋቾች ወደ ሜዳ የተመለሱት መቐለዎች ቀላል የማይባል ፈተናን በሲዳማ ቡና ላይ ፈጥረው ቢታዩም ጎል እና መረብ በሌላ ጎል መሟሸት ሳይችል ጨዋታው 1ለ0 በመጠናቀቁ ሲዳማ ቡና መሪነቱን ማጠናከር ችሏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...