ከብሔራዊ ቡድን መልስ አራት ጨዋታዎች የተደረጉበት የሊጉ መርሀግብር በሦስት በአቻዎች በአንድ ድል ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች መልስ ዛሬ በ25ኛው ሳምንት መርሀግብር ሲመለስ አራት ጨዋታዎች ተደርገውበት አንዱ ብቻ ነው በድል የተጠናቀቀው የሜዳ ለውጥ ተደርጎበት አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ የተከናወነው የኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ባህርዳር ከተማ መርሀግብር ያለ ጎል ሲጠናቀቅ ላለመውረድ እየተፍጨረጨረ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ግን ድል ቀንቶታል። 24ኛው ደቂቃ ላይ ኤፍሬም ታምራት ከማዕዘን ያሻማውን ኳስ የመጀመሪያ ጨዋታውን ያደረገው የአጋማሹ አዲሱ ሴኔጋላዊ አማካይ ማማዱ ሴክ በግንባር ገጭቾ ቡድኑን መሪ ማድረግ ሲችል እንደነበራቸው ብልጫ ከአስር ደቂቃዎች በኋላም ሁለተኛውን ጎል አስቆጥረዋል። ኤፍሬም ታምራም ከግራ የሜዳው ክፍል ለአሸናፊ ተገኝ መሬት ለመሬት ወደ ሳጥን የላካትን ኳስ ገዛኸኝ ደሳለኝ ኳሷን ለማውጣት ጥረት ሲያደርግ በራሱ መረብ ላይ አሳርፏታል።

ከዕረፍት መልስ ከነበረባቸው ችግሮች ተሻሽለው መመለስ የቻሉት ሸገር ከተማዎች 56ኛው ደቂቃ ሔኖክ አዱኛ ከማዕዘን አሻምቶ ቢኒያም ፍቅሩ በግንባር ገጭቶ መረቡ ላይ ያሳረፋት ብቸኛ ጎል ቡድኑን መታደግ ሳትችል አርባምንጭ ከተማ 2ለ1 አሸናፊ አድርጓል።
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ዘጠኝ ሰዓት ላይ ድሬዳዋ ከተማን ከፋሲል ከነማ ያገናኘው መርሀግብር አሰልቺ ይዘትን ተላብሶ በሙከራዎች መድመቅ ተስኖት ጎል ሳይቆጠርበት 0ለ0 መጠናቀቅ የቻለ ነበር። ከጨዋታው ይልቅ ግን የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋቾች ከጡረታ አቆራረጥ ጋር በተያያዘ ገሚሱ ተጫዋች በቂ ልምምድን ሳይሰሩ በጨዋታው የቀረቡ ሲሆን ከጨዋታውም ይልቅ ትኩረት የሚስበው ጉዳይ ይሄ እንደነበር መናገር ይቻላል።

ሌላኛው ምሽቱን በአዳማ በነበሩበት ሆቴል የአልጋ እና የምግብ ሳይከፈል አትወጡም በሚል በሌላ በኩል ደግሞ ለተጫዋቾቹ የሁለት ወር ደመወዝ ሳይከፍል ትላንት ሀዋሳ ደርሶ በሆቴል ውስጥ የማላቀቂያ ልምምድ የተሰሩት ምድረ ገነት ሽረ ከመቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 አጠናቀዋል። መቻሎች ፍፁም ብልጫን ባሳዩበት እና በዕለቱ ዋና ዳኛ ሙሉቀን ያረጋል ሁለት የፍፁም ቅጣት ምት በተከለከሉባቸው የመጀመሪያው አጋማሽ እንዳሳዩት የበላይነት ግን የግብ ዘቡን መክብብ ደገፉን የኋላ በር ማስከፈት ሳይችል ቀርተዋል።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታውን በመቆጣጠር የጀመሩት መቻሎች 50ኛው ደቂቃ ፈቱዲን ጀማል ከቀኝ መስመር ወደ ሳጥን ያሻማውን ኳስ ብሩክ ማርቆስ በግንባር አመቻችቶለት ዓለምብርሀን ይግዛው በእግሩ ወጋ አድርጎ በማስቆጠር ቡድኑ መሪ ማድረግ ችሏል። ጨዋታው ቀጥሎ የመቻልን መቀዛቀዝ ተከትሎ ወደ ጨዋታ የገቡት ምድረ ገነት ሽረዎች 77ኛው ደቂቃ ግሩም ጎል አግኝተዋል። ናትናኤል ተክላይ ላይ ብሩክ ማርቆስ የሰራውን ጥፋት ተከትሎ የሰጠውን የቅጣት ምት ተካልኝ ደጀኔ አሊዮንዚ ናፊያን መረብ ላይ በማስቆጠር በመጨረሻም ጨዋታው 1ለ1 ተጠናቋል።
አስተያየት ይስጡ