በካናዳ ፕሪምየር ሊግ ከደመቁ ተጫዋቾች መካከል አንዱን ተጫዋቾች ይዘንላችሁ ቀርበናል።
አባቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ እናቱ ደግሞ የካናዳ ዜግነት ያላት እንስት ነች እርሱም የተወለደው ከሀያ አንድ አመት በፊት በካናዳዋ ቶሮንቶ ኦናታሪዮ ውስጥ ሲሆን አሁን የምነግራችሁ በዋናነት የሚጫወትበት በመሐል ተከላካይ ቦታ ላይ ቢሆንም በቀኝ እና በግራ መስመር ቦታ ላይም መጫወት ይችላል። ሙሉ ስሙ ኖሀ አብርሀም ሰውነት አባትነህ ሲሆን በእግር ኳሱ አለም ግን ኖሀ አባትነህ በሚል ስሙ ይታወቃል።

እግር ኳስን የጀመረው ገና የአምስት አመት ልጅ በነበረበት ወቅት ሲሆን በዛው ካናዳ ቅዱስ አንቶኒ ጣሊያን ማሰልጠኛ ውስጥ ቢሆንም በፍጥነት በነበረው ዕድገት ወደ እንግሊዞቹ አርሰናል ወይም ፉልሀም የማምራት ዕድል ገና በአስር አመት የነበረው ቢሆንም ወደ ጣሊያን በማምራት በሳቪዮ ፣ በታላቁ ሮማ እንዲሁም በይበልጥ በታወቀበት ላዚዮ ከ17 ከ18 እና ከ19 በታች ቡድኖች ውስጥ እንዲሁም በሌሎቹ የጣሊያን የታችኛው ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች ላሜዚያ እና ካምቦ ዳሬስጎ ተጫውቷል።
በድጋሚ ወደ ጣሊያን ሴሪ ኣው ክለብ ላዚዮ ዋናው ቡድን የማደግ ዕድል የነበረው አንድ ሜትር ከዘጠና ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ይህ ወጣት ተከላካይ ወደ ካናዳ ከተመለሰም በኋላ ለዮርክ ዩናይትድ እና ያለፉትን ሦስት አመታት ደግሞ በካናዳ ፕሪምየር ሊግ ለሚካፈለው ለአትሌቲኮ ኦቶዋ በመጫወት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከሀያ አመት በታች ብሔራዊ ቡድኗ ከተጫወተላት ካናዳ ይልቅ የአባቱን ሀገር ኢትዮጵያን በተለያዩ የእግር ኳስ ውድድሮች ማገልገልን እንደሚፈልግ ጠቁሞናል።
አስተያየት ይስጡ