በኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች የሴካፋው ብሔራዊ ቡድን የደመቁት ሁለቱ ተጫዋቾች ወደ አፍሪካ ዋንጫው አያመሩም።
የአሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመሩ ከ17 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አውራ መሆን የቻሉት አጥቂው ዳዊት ካሳው እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ቢኒያም አብርሀ በዕድሜ ምክንያት ከአፍሪካ ዋንጫ መድረክ ውጪ ሆነዋል።

በሞሮኮ እንደሚስተናገድ ማረጋገጫ የተሰጠው ከ17 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ሌሎች 3 ተጨማሪ ተጫዋቾች ከMRI ምርመራ በኋላ ከውድድሩ ውጪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተሳክቶለት ወደ አለም ዋንጫው ከተጓዘ ግን የተጫዋቾቹን ግልጋሎት ሀገራችን ማግኘት ትችላለች።
አስተያየት ይስጡ