በሜጀር ሊግ ሶከር የአለም ኮከቡ ሊዮኔል ሜሲን በተቃራኒው የገጠመው ቁመታሙ ተከላካይ።


ስሙ ኒኮሲ ተፈሪ ይባላል አባቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ እናቱ ደግሞ የማዳጋስካር ዜግነት አላት። በአሜሪካ ኒዮርክ ከተማ ልዩ ስሟ ማንሀታን ተብላ በምትጠራ አካባቢ የተወለደው ይህ አንድ ሜትር ከዘጠና ሦስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ይህ ቁመታም የመሐል ተከላካይ እግር ኳስን በዛው በአሜሪካ የኮሌጅ እግር ኳስ ክለቦች በሆኑት አንኮን ሀስኪስ እና ሪድ ሀውክስ መጀመር የቻለ ሲሆን በመቀጠልም በአሜሪካ MLS ሊግ ላይ በሚካፈለው ኖርዝ ቴክሳስ እየተጫወተ ባሳየው አስደናቂ አቋም ዳላስ ክለብን በመቀላቀል በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ላይ በ2020 የአውሮፓውያን አቆጣጠር ጀምሮ መጫወትን የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከሩ ሎሳንጀለስ ጋላክሲ ወይም ኤል ኤፍሲ እየተባለ በሚጠራው ክለብ ውስጥ እየተጫወተ ከአለማችን ምርጡ አጥቂ ሊዮኔል ሜሲ ጋር በተቃራኒው እየተፋለመ በሊጉ አስደናቂ አቋሙን እያሳየ ይገኛል።

በቅርቡ ለአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ተደርጎለት ማሌዥያን በገጠመው ቡድኗ ውስጥ ተካቶ የወዳጅነት ጨዋታን ተሰልፎ ማድረግ የቻለው ግዙፉ ተከላካይ የአባቱን ሀገር ኢትዮጵያን መለያዋን ለብሶ መጫወት ፅኑ እምነቱ እንደሆነ አጥብቆ ይገልፃል።
አስተያየት ይስጡ