ስሪ ፖይንት አካዳሚን ለኢትዮጵያ ካበረከቱልን ኢትዮጵያዊ የተገኘው በጀርመን ቡንደስሊጋ የነገሰው እና አሁን በቱርክ ሱፐር ሊግ የሚጫወተው ግዙፉን አጥቂ አሁን እናስተዋውቃችሁ።


አሁን የምነግራችሁ ተጫዋች በጀርመን ቡንደስሊጋ በተደጋጋሚ ስሙ ሲጠራ የሰማችሁትን ታዋቂ አጥቂ ነው። ስሙ ዴቪድ ሰልኬ ይባላል የተወለደው በጀርመኗ ሾርን ዶርፍ ከተማ ሲሆን አባቱ ኢትዮጵያዊው ቴዲ ሩፕ ሲሆኑ እናቱ ደግሞ የቼክ ሪፐብሊክ ዜግነት ያላት አንድሬያ ሰልኬ ትባላለች።

በጀርመኑ ስቱትጋርት ማሰልጠኛ ውስጥ የልጅነት ጊዜውን በእግር ኳስ ስልጠና ያሳለፈው አንድ ሜትር ከዘጠና አምስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ይህ ግዙፍ አጥቂ በመቀጠልም በእግር ኳስ ህይወቱ በኖርማኒያ እና ሆፈኒየም የወጣት ቡድኖች ውስጥ ከተጫወተ በኋላ በኋላም የጀርመን ቡንደስሊጋውን ክለብ ወርደር ብሬመንን ተቀላቅሎ ከብዙሀኑ የጀርመን ማህበረሰብ ጋር ለመተዋወቅ በቃ እኛ ኢትዮጵያዊያን ጠንቅቀን ለምናውቃቸው ለሌሎቹ ለጀመርኖቹ አርቪ ላይቭዚሽ ፣ ህርታ በርሊን ፣ ኮሎኝ እና ሀምቡርግ ክለቦች በመጫወት በሀገሪቷ ሊግ አቅሙን በደንብ ያሳየው ይህ አጥቂ በጀርመን ቆይታውም በ299 ጨዋታዎች 78 ጎሎችን በተቃራኒ ቡድን መረብ ላይ ማሳረፍ የቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ደግሞ በቱርክ ሱፐር ሊጉ ክለብ ኢስታንቡል ባሻክሻየር በመጫወት ላይ ይገኛል።

ለተወለደባት ጀርመን ከ16 ፣ ከ17 ፣ ከ18 ፣ ከ19 ፣ ከ21 አመት በታች እና ለኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድኖቿ ጭምር በመሰለፍ በድምሩ 33 ጎሎችን ያስቆጠረው ይህ ቁመታም አጥቂ አባቱ አቶ ቴዲ ሩፕ ልጃቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት ለማድረግ ብርቱ ጥረትን ያደረጉ ሲሆን ስሪ ፖይንት የተባለን ከመላው ኢትዮጵያ የተመረጡ ታዳጊዎች የሚሰለጥኑበትን የእግር ኳስ አካዳሚ ሀገራችን ውስጥ የመሠረቱ ሲሆን እንግሊዛዊ አሰልጣኝ ቀጥረው ኢትዮጵያዊያን ታዳጊዎች እንዲሰለጥኑ አድርገዋል። ቅርቡ በኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ውስጥ የደመቁትን እንደ ዳዊት ካሳው እና ቢኒያም መሐሪ አይነት ተጫዋቾች እሳቸው በመሠረቱት ስሪ ፖይንት አካዳሚ እንዲፈሩ ያደረጉት ጉሙቱው ኢትዮጵያዊው ሰው ልጃቸው ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲጫወት አሁንም ተስፋ እንዳላቸው ደጋግመው ይናገራሉ።

አስተያየት ይስጡ