መነሻ ገጽ ዋልያዎቹ “ተጫዋቾቹ ያላቸውን አቅም ለመስጠት 100% ዝግጁ ናቸው”
ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

“ተጫዋቾቹ ያላቸውን አቅም ለመስጠት 100% ዝግጁ ናቸው”

አጋራ
አጋራ

“የመጨረሻ አምስት ወይም ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች የተጫወተ መሆን ነበረበት”

“በቁጭት ነው እየሰራን ያለነው”

“አቅም ያለው ተጫዋች ነው የሚገባው ስም አይደለም”

==================

የብሔራዊ ቡድኑን ዝግጅት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል

===================

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የ2027 የአፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የደርሶ መልስ ጨዋታውን ለማድረግ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

ከሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ጨዋታዎቹን የሚያደርገው ብሔራዊ ቡድኑ ማረፊያውን በጁፒተር ሆቴል አድርጎ በአዲስ አበባ ስታድየም እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ላይ ዝግጅቱን በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ቀዳሚ ጨዋታውን ለማድረግም በነገው ዕለት ወደ ሞሮኮ ጉዞውን የሚያደርግ ሲሆን ከዛ አስቀድሞ አጠቃላይ ዝግጅቱን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቡድናቸው በጥሩ የአካል እና የአዕምሮ ዝግጁነት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከተጫዋቾች ምርጫቸው ጋር በተያያዘም አሰልጣኙ የምርጫ መስፈርታቸውን እንዲህ አብራርተዋል።

“ከሳኦ ቶሜ ጋር የምናደርገው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ነው። የጥሎ ማለፍ ጨዋታ የራሱ ባህሪ አለው። ለተጫዋቾች ልምድ የሚሰጥበት ወይንም ተጫዋቾችን በብዛት ለወደፊት የምንዘጋጅበት አይደለም። ስለዚህ ከባህሪው አንፃር በመነሳት ያንን አላማ በማድረግ ለዚህ ይጠቅሙናል የምንላቸውን ተጫዋቾች መርጠናል። ጥሎ ማለፍ እንደመሆኑ መጠን ልምድ ይጠይቃል። ሁለተኛ ጫናን የለመዱ ተጫዋቾች ይጠይቃል። ሶስተኛ ረጅም ጉዞ አለ የሱን ልምድ ይጠይቃል። በሰው ሀገር በተለየ አየር የመጫወት ልምድን ይጠይቃል። በተጨማሪም ባሉን አጭር ጊዜዎች የሚሰሩ ስራዎች ስለነበሩ የምንመርጣቸው ልጆች በአካል ብቃታቸው ብቁ የሆኑ መሆን ነበረባቸው። ያንንም ለማሟላት ቢያንስ የመጨረሻ አምስት ወይም ስድስት ተከታታይ ጨዋታዎች የተጫወተ መሆን ነበረበት።አካል ብቃት ወሳኝነት ስላለው።”

ከሀገር ውጪ የሚጫወቱት ጋቶች ፓኖም እና ከነአን ማርክነህ ከክለቦቻቸው እንደመጡ በቀጥታ ወደ ልምምድ መግባታቸውን ገልፀዋል።

ስለ ተጋጣሚው የሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ብሔራዊ ቡድን ሰፊ መረጃ እንደሌላቸው ያነሱት አሰልጣኝ ዮሐንስ በርካታ ተጫዋቾችን ከአውሮፓ መያዛቸውን በመግለፅ ነገር ግን በሜዳ ላይ ማድረግ የሚገባንን እናደርጋለን ፤ የሚወስነው 180 ደቂቃው ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በጨዋታ መንገድ ዙሪያ በፋሲል ከነማ ይዘው የቀረቡትን በብሔራዊ ቡድኑም ይደግሙ እንደሆን የተጠየቁት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ይህን ምላሽ ሰጥተዋል።

“ፋሲል ከነማ እና ይሄ አይገናኝም። አላማው ይሄ የጥሎ ማለፍ ውድድር ነው። ልጆቹ የተመረጡት ለጥሎ ማለፍ ውድድር ነው። አጭር ሁለት ጨዋታ ነው። ያ የሙሉ ውድድር ዓመት ጨዋታ ነው። አንድ ወሳኝ ጨዋታ ሲሆን እና አሰልጣኞች የምንዘጋጅበት መንገድ መንፈስ ይለያል ፤ አንድ አይሆንም።”

ከተጫዋቾች ዝግጁነት አንፃር ደግሞ ሁሉም ተጫዋቾች 100% ያላቸውን ለመስጠት ዝግጁ ናቸው ሲሉ በልበ ሙሉነት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ተናግረዋል።

የተጋጣሚ ቡድኑን ያነሰ ግምት ሳይሰጡ ወደ ሜዳ ከመግባት አንፃር ለቀረበላቸው ጥያቄ ተጫዋቾች በላቀ የስነ ልቦና ዝግጅት በልዩ ትኩረት ነው ዝግጅታቸውን እያደረጉ ነው የሚገኙት ሲሉ ገልፀዋል።

አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳቦችን ያነሱት የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን የመልሱ ጨዋታ ድሬዳዋ ስታዲየም ላይ እንዲደረግ ሰፊ ጥረቶች መደረጋቸውን ገልፀዋል።

ከካፍ የተሰጡ ግብረ መልሶችን ማሳሰቢያዎችን በማንሳትም ማስተካከያዎች መደረጋቸውን ያነሱ ሲሆን ከዚህም መካከል የጎሉ ቋሚ እንዲቀየር መደረጉን ተናግረዋል።

የግምገማው ውጤት ተስፋ አስቆራጭ ነበር ሲሉ ያነሱት አቶ ባህሩ ጥላሁን ፌዴሬሽኑ ጨዋታው እዚህ እንዲደረግ ካለው ፍላጎት የተነሳ በተደረጉ ጥረቶች መሳካቱን አውስተዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...