ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ አራተኛውን የአጋማሹን አዲስ ፈራሚ በእጃቸው አስገብተዋል።
በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ የሚመሩት እና በአጋማሹ የዝውውር መስኮት ጌቱ ሀይለማርያም ፣ አፈወርቅ ሐይሉ እና ተመስገን መንገሻን ቀደም ብለው ያስፈረሙት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ቡድናቸውን በሊጉ እንዲቆይ ይረዳቸው ዘንድ ግዙፉን ናይጄሪያዊውን የ23 አመት ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለትን አጥቂው ሳሙኤል አያንሪንዴን ማስፈረማቸውን ባገኘሁት ማጣራት ለማረጋገጥ ችለናል።
በሀገሩ ክለብ ሹቲንግ ስታር ፣ ኩዋራ ዩናይትድ እና ስፖርቲንግ ሌጎስ መጫወት የቻለው በጎረቤት ሀገር ለኬኒያ ፓሊስ ሲጫወት የነበረው አንድ ሜትር ከሰባ ዘጠኝ የሚረዝመው ይህ አጥቂ በይፋ አዲሱ የክለቡ ተጫዋች መሆኑን ለማወቅ ችለናል።
አስተያየት ይስጡ