መነሻ ገጽ ዜናዎች የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ2016 ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔ!

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ግንቦት 05 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

በሳምንቱ መርሃ ግብር በተደረጉ ጨዋታዎች አምስት በመሸናነፍ ቀሪ ሶስቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ 17 ጎሎች በ15 ተጫዋቾች ተቆጥረዋል። 25 ቢጫ ካርድ ለተጫዋቾችና ቡድን አመራሮች ሲሰጥ አንድ ቀይ ካርድ ተመዝግቧል።

በሳምንቱ በአምስት ተጫዋቾች ላይ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል። አዲስ ግደይ(ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ መሳይ አገኘሁ(ባህርዳር ከተማ)፣ ብሩክ ማርቆስ(ሀዲያ ሆሳዕና) እና ዳዋ ሆጤሳ(ሀዲያ ሆሳዕና) በሳምንቱ ጨዋታ አምስተኛ የጨዋታ ቢጫ ካርድ በመመልከታቸው ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ፤ ናትናኤል ናሴሮ(ወላይታ ድቻ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ በቀይ ካርድ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ተወስኗል።

በተጨማሪም ለወላይታ ድቻ እና ሲዳማ ቡና የቡድን መሪዎች የፕሪምየር ሊጉ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ በቀጣይ ቀናት ለማነጋገር ጥሪ አስተላልፏል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...