መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከወራት በኋላ ሐምሌ 12 ሸገር ደርቢ በአሜሪካ ይደረጋል !
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ከወራት በኋላ ሐምሌ 12 ሸገር ደርቢ በአሜሪካ ይደረጋል !

አጋራ
አጋራ

● ሱራፌል ዳኛቸዉ የሶስት አመት ኮንትራት ከአሜሪካዉ ክለብ ጋር ተፈራርሟል !!

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የዲሲ ዩናይትድ ይፋዊ የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት ከደቂቃዎች በፊት በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲከናወን የስምምነት ፊርማ ከተከወነባቸዉ ጉዳዮች መካከልም :-

– የአሜሪካዉ ሜጀር ሊግ ሶከር ተሳታፊ የሆነው ዲሲ ዩናይትድ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን በመጪው ሐምሌ ወርም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ አቅንቶ ከክለቡ ጋር የጉብኝት እና የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርግ በስምምነቱ ላይ ተጠቅሷል ።

– በተጨማሪም በምሽቱ ከነበሩ ስምምነቶች መካከል ከሳምንት በፊት በዱባይ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ የቻሉት ሁለቱ የመዲናይቱ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ባደረጉት ስምምነት መሰረት ከወራት በኋላ ሐምሌ 12 ወደ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አምርተው የእርስ በእርስ የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል ።

– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቀድሞ ፋሲል ከነማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸዉም ከአሜሪካዉ ክለብ ዲሲ ዩናይትድ መጋቢ ከሆነዉ ክለብ ሉደን ዩናይትድ ጋር የሶስት አመታት ኮንትራቱን በይፋ በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ተፈራርሟል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...