● ሱራፌል ዳኛቸዉ የሶስት አመት ኮንትራት ከአሜሪካዉ ክለብ ጋር ተፈራርሟል !!
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የዲሲ ዩናይትድ ይፋዊ የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት ከደቂቃዎች በፊት በሸራተን አዲስ ሆቴል ሲከናወን የስምምነት ፊርማ ከተከወነባቸዉ ጉዳዮች መካከልም :-
– የአሜሪካዉ ሜጀር ሊግ ሶከር ተሳታፊ የሆነው ዲሲ ዩናይትድ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን በመጪው ሐምሌ ወርም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ አሜሪካ አቅንቶ ከክለቡ ጋር የጉብኝት እና የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርግ በስምምነቱ ላይ ተጠቅሷል ።
– በተጨማሪም በምሽቱ ከነበሩ ስምምነቶች መካከል ከሳምንት በፊት በዱባይ የወዳጅነት ጨዋታ ማድረግ የቻሉት ሁለቱ የመዲናይቱ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ከዲሲ ዩናይትድ ጋር ባደረጉት ስምምነት መሰረት ከወራት በኋላ ሐምሌ 12 ወደ አሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ አምርተው የእርስ በእርስ የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያደርጉም ተመላክቷል ።
- ማሰታውቂያ -
– የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የቀድሞ ፋሲል ከነማ የመሐል ሜዳ ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸዉም ከአሜሪካዉ ክለብ ዲሲ ዩናይትድ መጋቢ ከሆነዉ ክለብ ሉደን ዩናይትድ ጋር የሶስት አመታት ኮንትራቱን በይፋ በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ተፈራርሟል ።