መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀድሞ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በSuper sport የቀጥታ ስርጭት በተንታኝነት….. !!
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የቀድሞ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በSuper sport የቀጥታ ስርጭት በተንታኝነት….. !!

አጋራ
አጋራ

በቀጣዩ አዲሱ የውድድር አመት በSuper sport የቀጥታ ስርጭት ላይ የቀድሞ እግርኳስ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በጨዋታ ተንታኝነት እንደሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ግልፅ አድርጓል።

በዚህም ባለፉት ሶስት ያህል አመታት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ባገኘዉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የተለያዩ የስፖርት ጋዜጠኞች በኮሜንታተርነት እና ተንታኝነት ሲሰሩ መቆየታቸዉ የሚታወስ ሲሆን ፤ አሁን ግን በተለይ ከቀጣይ አመት ጀምሮ የቀድሞ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተንታኝነት እንደሚሰሩ እና ከዚያ አስቀድሞም ለሚመረጡት ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ከሚዲያ ኢቲክስ ጋር ተያይዞ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከሚወስዱት ስልጠና በመቀጠልም ከሚመለከተዉ አካል ጋር የኮንትራት ፊርማ እንደሚፈራረሙ እና ሊጉም ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ በሚኖረዉ የጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ወቅት የተመረጡት የቀድሞዉ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተንታኝንት ተሳታፊ እንደሚሆኑ አክሲዮን ማህበሩ ያስታወቀ ሲሆን ፤ ይሄንን በተመለከተም ማህበሩ ለSuper sport ጉዳዩን በተመለከተ አቅጣጫ ማስቀመጡን አመራሮቹ አስታውቀዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...