በኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘዉ በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ዉድድር ላይ በዛሬው እለት በግማሽ ፍፃሜ ከኬንያው ቬጋ ኩዊንስ ጋር ጨዋታውን ያደረገዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች ቡድን 2-1 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ለፍፃሜ ጨዋታ ደርሷል።
ለእንስቶቹ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተሰጠዉ የጭማሪ ሰአት ሎዛ አበራ በ90+3 እና አረጋሽ ካልሳ በ95 ኛ ደቂቃ አከታትለዉ ባስቆጠሯቸዉ ግቦች አሸንፈዋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጪው እሮብ ከታንዛኒያዉ ጄ.ኬ.ቲ ኩዊንስ ጋር የፍፃሜዉን ጨዋታ የሚያደርግ ይሆናል።

- ማሰታውቂያ -