ከቀናት በፊት በይፋ ለፋሲል ከነማ ፊርማዉን ያኖረዉ የቀድሞዉ የቅዱስ ጊዮርጊሱ አማካሪ ጋቶች ፓኖም በዛሬው እለት አዲሱን ቡድኑን ተቀላቅሏል።
ፋሲል ከነማዎች ለ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን ቅድመ ዝግጅታቸዉን በሀዋሳ ከተማ እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን አዲሱ ፈራሚያቸዉ ጋቶች ፓኖም በዛሬው እለት ወደ ሀዋሳ ከተማ በመምጣት ቡድኑን ተቀላቅሏል።
- ማሰታውቂያ -
ከቀናት በፊት ፋሲል ከነማዎች በላይቤሪያዊው ክሌይመንት ሞሊ ካርፐህ በቀረበባቸዉ የደሞዝ ይከፈለኝ ክስ ምክንያት በFIFA ተጫዋቾችን እንዳያስፈርሙ እግድ እንደተጣለባቸዉ ይታወቃል።
አፄዎቹ ከ2016 ዓ.ም የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በማስቀደም የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ጎፈሬ የስፖርት ትጥቅ አምራች ድርጅት በመተባበር በሀዋሳ ከተማ ከሰኔ 3 ጀምሮ በ 8 ክለቦች መሀከል የሚያዘጋጁትን ሲዳማ ጎፈሬ ካፕን የሚሳተፉ ይሆናል።