በአሰልጣኝ ፍፁም በርሄ እየተመሩ የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ ሻምፒዮን በመሆን ወደ ኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ያደጉት የሲዳማ ቡና የሴቶች ቡድን ለ2016 ዓ.ም የዉድድር ዘመን አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም የጀመሩ ሲሆን በይፋ 5 አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ ቀላቅለዋል።
በዚህም መሰረት የቀኝ መስመር ተከላካይ የሆነችዋን ህይወት ዳንኤልን ከ ድሬዳዋ ፣ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነችዋን ማህሌት ተስፋዬን ከኢትዮጵያ አካዳሚ ፣ የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች የሆነችዋን ቤዛ ንጉሴን ከድሬዳዋ ፣ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነችዋን ሙና ከድርን ከቂርቆስ እንዲሁም የመሀል ተከላካይ የሆነችዋን ንጋት ጌታቸዉን ከልደታ እያንዳንዳቸዉን በ2 ሁለት ዓመት ኮንትራት ማስፈረም ችለዋል።
በቀጣይ ቀናትም አዳዲስ ክለቡን የሚቀላቀሉ ተጫዋቾች ያሉ ሲሆን ከእሱ ጎን ለጎን የነባር ተጫዋቾችን ዉል የማደስ ስራ እንደሚሰራ ለማወቅ ችለናል።