በቀጣዩ አዲሱ የውድድር አመት በSuper sport የቀጥታ ስርጭት ላይ የቀድሞ እግርኳስ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በጨዋታ ተንታኝነት እንደሚያገለግሉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማህበር ግልፅ አድርጓል።
በዚህም ባለፉት ሶስት ያህል አመታት የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ባገኘዉ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ የተለያዩ የስፖርት ጋዜጠኞች በኮሜንታተርነት እና ተንታኝነት ሲሰሩ መቆየታቸዉ የሚታወስ ሲሆን ፤ አሁን ግን በተለይ ከቀጣይ አመት ጀምሮ የቀድሞ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተንታኝነት እንደሚሰሩ እና ከዚያ አስቀድሞም ለሚመረጡት ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች ከሚዲያ ኢቲክስ ጋር ተያይዞ ስልጠና እንደሚሰጣቸው አቅጣጫ ተቀምጧል።
ከሚወስዱት ስልጠና በመቀጠልም ከሚመለከተዉ አካል ጋር የኮንትራት ፊርማ እንደሚፈራረሙ እና ሊጉም ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ በሚኖረዉ የጨዋታዎች የቀጥታ ስርጭት ወቅት የተመረጡት የቀድሞዉ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች በተንታኝንት ተሳታፊ እንደሚሆኑ አክሲዮን ማህበሩ ያስታወቀ ሲሆን ፤ ይሄንን በተመለከተም ማህበሩ ለSuper sport ጉዳዩን በተመለከተ አቅጣጫ ማስቀመጡን አመራሮቹ አስታውቀዋል።