ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ፕሪሚየር ሊጉ ዓርብ ይፈጸማል

አጋራ
አጋራ

👉የዕለተ አርቡ ጨዋታ በሶስት ስታዲየሞች
በተመሳሳይ ሰዓት ይካሄዳል…

👉ለክብር ዕንግዶች ለአርብ ጥሪ ተደርጓል…

👉 ዓርብ የሚተላለፈው አንድ ጨዋታ የማን እንደሆነ
አልታወቀም…

ሁለተኛው አመት የዲ ኤስ ቲቪ ዘመን የ2014 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዓርብ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ሶስት ጨዋታዎች ይፈጸማል።

ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ለዋንጫ የሚደረገው የቅዱስ ጊዮርጊስና የአዲስ አበባ ከተማ፣ የፋሲል ከተማና የድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም የሀዋሳና ከተማና የአዳማ ከተማ ጨዋታዎች ዓርብ የሚደረጉ ሲሆን ሶስቱም ጨዋታዎች በሶስት ስታዲየሞች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሊግ ኩባንያው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ጨዋታዎቹ በባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም፣ በባህርዳር ዩኒቨርስቲና በአጼ ቴዎድሮስ ስታዲየም ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ከ4..ከ7 ወይም ከ10 ሰዓት በአንዱ በተመሳሳይ ሰዓት ጨዋታው ይካሄዳል ተብሏል። እንደ መረጃ ምንጩ ከሆነ ቀኑ እንደማይለወጥና የፍጻሜው ጨዋታው ዓርብ እንደሚሆን የተነገረው ለክብር እንግዶች ጥሪ የተደረገው ለአርብ በመሆኑ ነው ተብሏል።

በመጨረሻው ሰዓት የቀጥታ ስርጭት የሚኖረው አንድ ጨዋታ ነው ተብሎ የነበረ ቢሆንም ዲ ኤስ ቲቪ ለቀረጻው በመስማማቱ ቀረጻው ይቀጥላል ተብሏል። ነገር ግን በሊጉ የውድድር ደንብ መሠረት በፍጻሜ ጨዋታው የቀጥታ ስርጭት የሚያገኘው የትኛው ጨዋታ እንደሆነ የሚገልጽ ምንም አይነት ደንብ ባለመኖሩ ከሁለቱ የዋንጫ ጨዋታ መሃል ስርጭቱ የሚተላለፈው የትኛው ጨዋታ ይሁን የሚለው ነገ በሚኖረው ስብሰባ ላይ ይወሰናል ተብሎ ይጠበቃል።

በውድድሩ የመጨረሻ ሳምንት መርሀ ግብር መሠረት ሀሙስ ወላይታ ድቻ ከወልቂጤ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ከሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም ቅዳሜ ጅማ አባጅፋር ከመከላከያ፣ ኢትዮጵያ ቡና ከባህርዳር ከተማ ሰበታ ከተማ ከእርባምንጭ እንደሚጫወቱ ከውስጥ አዋቂ የተገኘ መረጃ ያስረዳል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...