መነሻ ገጽ መከላከያ የጨዋታ ዘገባ | መከላከያ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸዉን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል።
መከላከያቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | መከላከያ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸዉን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል።

አጋራ
አጋራ

 

በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት ሶስተኛ ቀን የመጨረሻ ጨዋታ በደረጃ ሰንጠረዡ ከወገብ በታች ይገኙ የነበሩት መከላከያ እና አዳማ ከተማ ጨዋታቸውን በአቻ ዉጤት አጠናቀዋል።

እምብዛም ብርቱ ፍክክር እና በሙከራም ረገድ ይህ ነዉ ሊባል የሚችል በርከት ያለ ሙከራ ባልተመለከትንበት ጨዋታ መከላከያ ከአዳማ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ዉጤት ተገባዷል። ከመጀመሪያው ደቂቃ አንስቶ የተቀዛቀዘ በነበረዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም አልፎ አልፎ ከርቀት ወደ ተቃራኒ የግብ ክልል ይላኩ ከነበሩ ሙከራዎች ዉጭ ይህ ነዉ የሚባል ጠንካራ ሙከራን ለመመልከት 26 ደቂቃዎችን መጠበቅ ግድ ብሎን ነበር።

በዚሁ ደቂቃም ከአማኑኤል ጎበና የተቀበለውን ኳስ የፊት መስመር አጥቂዉ አሜ መሐመድ ወደ ግብ ለመቀየር በተቃረበበት ሰዓት የመከላከያዉ ተከላካይ አሚን ነስሩ በሸርታቴ ኳሷን አዉጥቷታል። በዚች አጋጣሚ ምናልባትም አዳማዎች መሪ ሊሆኑ የሚችሉበት ዕድል ነበር።

ከዚች ሙከራ በኋላ በተመሳሳይ የተቀዛቀዘ የጨዋታ መንገድ የቀጠለዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት ግን ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን አስመልክቶናል።

በጨዋታዉ 44ኛዉ ደቂቃ ላይ የአዳማ ከተማዉ የግራ መስመር ተከላካዩ ደስታ ዮሐንስ ከቅጣት ምት ጥሩ ሙከራን ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም ግብ ጠባቂው ክሌመንት ቦየ ግን እንደምንም አዉጥቶታል። ከአንድ ደቂቃ በኋላ ደግሞ ከእስራኤል እሸቱ የተቀበለዉን ኳስ ተሾመ በላቸዉ ወደ ግብ ቢሞክርም ኳሷ የግቡን አግዳሚ ነክታ ወደ ዉጭ ወጥታለች።

ከዕረፍት መልስ ጨዋታዉ ምንም እንኳን በተነቃቃ መንፈስ የተጀመረ ቢመስልም በጊዜ ሂደት እየተቀዛቀዘ ሂዶ ያን ያህል ለአይን ማራኪ ሳይሆን እና ይህ ነዉ የሚባል አደገኛ ሙከራ ሳያስመለክተን እስከ 75ኛዉ ደቂቃ ድረስ ቆይቷል። በዚሁ ደቂቃም ከአሜ መሐመድ የተቀበለውን ኳስ አብዲሳ ጀማል የመከላከያ ተከላካዮችን አታሎ ሳጥን ዉስጥ ከገባ በኋላ ወደ ግብነት ቀየረወለ ሲባል ግን አሚን ነስሩ ደርሶበት በሸርታቴ ኳሷን አዉጥቷታል።

ምንም እንኳን ጠንካራ ባይሆኑም በተደጋጋሚ የሚጥቃት ሀይላቸዉን ሲጠቀሙ እና እና የተወሰኑ ሙከራዎች ሲያደርጉ የተስተዋሉት አዳማ ከተማዎች ተሳክቶላቸው ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል። በተመሳሳይ የጨዋታው ሰዓት እየገፋ በሔደ ቁጥር ወደ ራሳቸዉ የግብ ክልል አፈግፍገዉ በመጫወት ሲያሳልፉ የነበሩት መከላከያዎችም በጨዋታው አንድም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ዉጤት ተጠናቋል።

ዉጤቱን ተከትሎም መከላከያ በ34 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአንፃሩ አዳማ ከተማ ደግሞ በ31 ነጥብ 13ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...