መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | ወላይታ ድቻ ከአስራ አንድ ጨዋታዎች በኋላ አሸንፏል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ዘገባ | ወላይታ ድቻ ከአስራ አንድ ጨዋታዎች በኋላ አሸንፏል

አጋራ
አጋራ

የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 28ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ ቀዳሚ ጨዋታ ጅማ አባጅፋርን ከወላይታ ድቻ አገናኝቶ ጅማ አባጅፋሮች በመስዑድ መሀመድ ግብ ሲመሩ ቢቆይም ከእረፍት መልስ በተቆጠሩ ሁለት ግቦች የጦና ንቦቹ አሸናፊ መሆን ችለዋል ።

ጅማ አባጅፋሮች በ27ኛው ሳምንት በሲዳማ ቡና በተረቱበት ጨዋታ ላይ ከነበረው የመጀመሪያ አሰላለፍ ሶስት ለውጦቶችን በማድረግ በአካሉ አትሞ ዳዊት እስጢፋኖስ እኔ በላይ ዓባይነል ምትክ የአብስራ ሙሉጌታ ፤ ሱራፌል ዐወል እና ቦና አሊን በቋሚ አሰላለፉ ማካተት ሲችለለ በወላይታ ድቻ በኩል ደግሞ በሳምንቱ በአዲስ አበባ ከተማ በተረቱበት ጨዋታ የነበረውን ምርጥ 11 ሙሉ ለሙሉ ተጠቅሟል ።

በጨዋታው የመጀመሪያ ደቂቃዎች ላይ ወላይታ ድቻዎች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የነበራቸው ሲሆን የማጥቃት ሂደታቸውን በአመዛኙ በመስመሮች በኩል በማድረግ ከሁለቱም አቅጣጫዎች በሚሻገሩ ኳሶች የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር የጣሩበት ነበር ። ምንም እንኳን ተሻጋሪ ኳሶቹ በትክክል ኢላማቸውን ማግኘት የቻሉ ባይሆኑም ።

ጅማ አባጅፋሮች ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ በጥሩ የኳስ ቅብብሎች ወደ ወላይታ ድቻ የግብ ክልል ለመደረስ የቻሉባቸውን አጋጣሚዎች መፍጠር ችለዋል ።

በ17ኛው ደቂቃ ላይም ጅማ አባጅፋሮች አስቆጪ ዕድል አምክነዋል ። ከግራ መስመር አቅጣጫ የተሻገረውን ኳስ መስዑድ መሀመድ በግሩም ሁኔታ አረጋግቶ የደረሰው ሱራፌል ጌታቸው አክርሮ የመታው ኳስ ከግቡ አናት በላይ ወጥቷል ።

በ24ኛው ደቂቃ ላይ መስዑድ መሀመድ ከርቀት አክርሮ ወደ ግብ የመታው ኳስ በአስደናቂ ሁኔታ የግቡን አግዳሚ ገጭቶ ከመረብ ላይ አርፏል ።

ከውሀ እረፍት መልስ ጅማ አባጅፋሮች በተሻለ የኳስ ቁጥጥር መጫወት የቻሉ ሲሆን ወደ ወላይታ ድቻ የግብ ክልል ለመድረስ እና ተጨማሪ የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያደርጓቸው ሙከራዎች በወላይታ ድቻ ተከላካዮች በቀላሉ ይነጠቁ ነበር ።

በወላይታ ድቻ በኩል ጅማ አባጅፋሮች በማጥቃት ሂደት ወቅቶ ጥለው የሚሄዷቸው ክፍተቶች ለመጠቀም ጥረቶቾን ቢያደርጉም ቃልኪዳን ዘላለም በ44ኛው ደቂቃ ላይ በሳጥኑ የግራ አቅጣጫ ወደ ግብ ሞክሮ አላዛር ማርቆስ ከያዘው ኳስ ውጪ ይህ ነው ሊባል የሚችል የግብ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም ነበር ።

የሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ከተጀመረ በአራተኛው ደቂቃ ላይ የጦና ንቦቹ አቻ የሆኑበትን ግብ አስቆጥረዋል ። ያሬድ ዳዊት ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ ነፃ የነበረው አበባየሁ ሀጂሶ በግንባር በመግጨት 49ኛው ደቂቃ ላይ የጨዋታው ውጤት ወደ 1 – 1 መቀየር ችሏል ።

ጅማ አባጅፋሮቾ ግብ ከማስተናገዳቸው ባለፈም ግቡን ያስቆጠረላቸው እና በጨዋታ እንቅስቃሴም የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መስዑድ መሀመድን በጉዳቴ ምክንያት በአጋማሹ ይዘውት ሳይገቡ ቀርተዋል ። በምትኩም ሙሴ ከበላ ተቀይሮ ገብቷል ።

አብዛኛው የአጋማሹ ክፍለ ጊዜ ተመጣጣኝ ሊባል የሚችል እንቅስቃሴ የታየበት ነበር ።

ጅማ አባጅፋሮች ወደ ወላይታ ድቻ የግብ ክልል ለመድረስ ጥረቶችን ማድረግ የቻሉ ሲሆን በተለይም ደግሞ ከመስመር በሚነሱ ኳሶች ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረዋል ። በአጋማሹ የመጀመሪያ ሙከራቸውም ከግራ መሰመር የተሻገረውን ኳስ መሀመድኑር ናስር በግንባር ገጭቶ ወደ ግብ ቢልከውም ቢንያም ገነቱ ተቆጣጥሮታል ።

የጦና ንቦቹ ቀዝቀዝ ብለው ባሳለፉባቸው ደቂቃዎች ላይ በአበባየሁ ሀጂሶ አማካኝነት ከሳጥን ውጪ ያደረጉትን ሙከራ አላዛር ማርቆስ መያዝ ችሏል ።

በ77ኛው ደቂቃ ላይ ግብ ጠባቂው ቢንያም ገነቱ በረጅም የመታውን ኳስ ስንታየሁ መንግስቱ በግንባር ወደ ኋላ አሳልፎት ቢንያም ፍቅሬ በፍጥነት ከተከላካዮች ጀርባ ግበቶ ኳሱን ለማግኘት በሚጥርበት ጊዜ አላዛር ማርቆስ ከግቡ ወጥቶ ኳሱን አርቆታል ።

83ኛው ደቂቃ ላይ ከቅጣት ምት የተሻገረን ኳስ አበባየሁ ሀጂሶ በመቀስ ምት ለማስቆጠር ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል ። ከአንድ ደቂቃ በኋላ በተቃራኒው መሀመድኑር ናስር ከርቀት አክርሮ ወደ ግብ የመታውን ኳስ ቢንያም ገነቱ ግብ ከመሆን አድኖታል ።

ከአራት ደቂቃዎች በኋላ ግን የጦና ንቦቹ አሸናፊ የሆኑበትን እና የጅማ አባጅፋሮትን ቅሰም የሰበረ ግብ አስቆጠረዋል ። ከራሳቸው የሜዳ ክፍል በረጅም የተሻገረውን ኳስ ስንታየሁ መንግስቱ በግንባር ገጭቶ ወደ ኋላ የላከውን ኳስ ቢንያም ፍቅሬ የተስፋዬ መላኩ ስህተት ታክሎበት በአላዛር ማርቆስ መረብ ላይ አሳርፎታል ።

በመጨረሻም ወላይታ ድቻ 2 ጅማ አባጅፈር 1 ሆኖ ጨዋታው ተጠናቋል ።

 

ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ ነጥቡን 41 በማድረስ ወደ 5ኛ ደረጃ ከፍ ሲል ጅማ አባጅፋር በበኩሉ በ23 ነጥቦች በ15ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል ።

በ29ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመጪው ሰኔ 19 ( ዕሁድ ) ረፋድ 4:00 ላይ ጅማ አባጅፋር ከወልቂጤ ከተማ ሲጫወት ቀጥሎ 7:00 ላይ ደግሞ ወላይታ ድቻ ሀድያ ሆሳዕናን የሚገጠም ይሆናል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...