መነሻ ገጽ ሊግ ካምፓኒ የኢት. እግርኳስ ፌዴሬሽንና ሊግ ኩባንያው ስምምነት ላይ ደርሰዋል
ሊግ ካምፓኒቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የኢት. እግርኳስ ፌዴሬሽንና ሊግ ኩባንያው ስምምነት ላይ ደርሰዋል

አጋራ
አጋራ

👉… ሊግ በሊግ ኩባንያው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ
ሙሉ ሃላፊነት ይቀጥላል…

👉… ጌታነህ ከበደም በቀጣዩ ጨዋታ አይሰለፍም…

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር በመሃላቸው የተፈጠረውን የመብት የማስከበርና የባለቤትነት አለመግባባት ወደከፋ ደረጃና እግርኳሱን ወደ መበጥበጥ ሳይደርስ ልዩነቶቻቸውን በውይይት ማስወገዳቸው ተገለጸ።

ከቀናት በፊት የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴ በወልቂጤ ከተማው ጌታነህ ከበደ ዙሪያ የሰጠውን ብይን የሊግ ኩባንያው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ እንደማይቀበለው ከገለጸ በኋላ በመሃላቸው ከፍተኛ ቅሬታ ከመከሰቱም በላይ ፌዴሬሽኑ በዋና ጸሃፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን ፊርማ ለሊግ ኩባንያው በላኩት ደብዳቤ ፌዴሬሽኑ ለአክሲዮን ማህበሩ ሰጥቶት የነበረውን ውክልና መሻሩን ተከትሎ ሊግ ኩባንያው ጋዜጣዊ መግለጫ መጥራቱ ይታወሳል።

ሊግ ኩባንያው ጋዜጣዊ መግለጫውን መጥራቱ ከታወቀ በኋላ የፌዴሬሽኑና የሊግ ኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች ተወያይተው ሊግ ኩባንያው መግለጫውን አራዝሞ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ወገኖች ባሉበት ለምክክር እንዲቀመጡ በተስማሙት መሰረት በፌዴሬሽኑ በኩል ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራ፣ ዋና ጸሃፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን በሊግ ኩባንያው በኩል የቦርድ ሰብሳቢው መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ፣ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ክፍሌ ሰይፈ፣ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢው ዶ/ር ወገኔ ዋልታንጉስን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሁለቱም ወገኖች ባለሙያዎች ትላንት ተገናኝተው ልዩነቶቻቸውን ያስወገዱበትን ውይይት አድርገዋል ተብሏል። በውይይቱ መሠረት ፌዴሬሽኑ የላከው የዕገዳ ደብዳቤ ውሳኔው ተሽሮ ውድድሩ በነበረበት የሊግ ኩባንያው ሃላፊነት እንዲቀጥልና የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተፈራ ደንበል የሊግ ኩባንያው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ የሚወስናቸውን የዲሲፕሊን ውሳኔዎች እንዲከታተሉ ፌዴሬሽኑን ወክለው የሊግ ኮሚቴ የውድድርና ስነስርዓት ኮማቴ ውስጥ የተወከሉት አቶ አበራ ሀብቴ ከወከሉት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ጋር ተናበው እየሰሩ አይደለም በሚል የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዲሰጣቸው መወሰኑን ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል።

በሁለቱ ወገኖች ስምምነት መሠረት ቀሪዎቹ 24 ጨዋታዎች በዶክተር ወገኔ ዋልታንጉስ በሚመራው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ስር እንዲቀጥልና የዚህ አለመግባባት መነሻ የነበረው የወልቂጤ ከተማ ተጨዋች የሆነው የጌታነህ ከበደ ጉዳይም በሊግ ኩባንያ በተቀመጠው አቅጣጫ እንዲቀጥል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በዚህ መሠረት ሁሉም የዲሲፕሊን ጉዳዮችን የሚያየው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ የ27ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ ውጤቶችን የማጽደቅ የዳኞችና ኮሚሽነሮችን ሪፖርት ተመልክቶ ውሳኔ ለመስጠት እንደተለመደው ዛሬ ጠዋት 4 ሰዓት ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል።

ሁለቱም ወገኖች በየፊናቸው አቋማቸውን ከመግለጽ ተቆጥበው ልዩነቶቻቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት በመቻላቸው ሊደነቁና ሊበረታቱ የሚገባበት ጉዳይ ነው ሲል ምንጫችን ገልጿል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...