ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስራ ሰባተኛ ሳምንት በሸገር ደርቢ ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ይገናኛል ።
ኢትዮጵያ ቡና ዊሊያም ሰለሞንን በጡንቻ መሳሳብ አቤል እንዳለን እና ወንድሜነህ ደረጀን ደግሞ በጉልበት ጉዳት ምክንያት በነገው የደርቢ ጨዋታ አገልግሎታቸውን አያገኝም።
ዊሊያም ሰለሞን ከሲዳማ ቡናው ጨዋታ በኋላ አንድ ልምምድ ከሰራ በኋላ ጉዳት አጋጥሞታል ።እንዲሁም ወንድሜነህ ደረጀም በልምምድ ላይ ነው ጉዳት ያጋጠመው። አቤል እንዳለ ከሲዳማ ቡና ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ ተቀይሮ መውጣቱ ይታወቃል ።ከጉዳቱ ማገገም ባለመቻሉ ከነገው ጨዋታ ውጪ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ