መነሻ ገጽ ዜናዎች ለይበልጣል ኤሊያስ የገቢ ማሰባሰቢያ በእውቅ ጋዜጠኞች እና በሶዶ ከተማ በሚገኙ ጤና ቡድኖች ምርጥ ስብስብ ጋር ጨዋታቸውን በሶዶ ስታዲየም አድርገዋል
ዜናዎች

ለይበልጣል ኤሊያስ የገቢ ማሰባሰቢያ በእውቅ ጋዜጠኞች እና በሶዶ ከተማ በሚገኙ ጤና ቡድኖች ምርጥ ስብስብ ጋር ጨዋታቸውን በሶዶ ስታዲየም አድርገዋል

አጋራ
አጋራ

ለባርሴሎና ቢ አካዳሚ ለመጫወት ለሁለት አመት ፊርማውን ላኖረው ይበልጣል ኤልያስ የገቢ ማሰባሰቢያ በእውቅ ጋዜጠኞች እና በሶዶ ከተማ በሚገኙ ጤና ቡድኖች ምርጥ ስብስብ ጋር ጨዋታቸውን በሶዶ ስታዲየም አድርገዋል ።

በጨዋታውም የሶዶ ጤና ቡድኖች ምርጥ እውቅ ጋዜጠኞችን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት አሸንፏል።ለእውቅ ጋዜጠኞች የስፖርት ዞን አዘጋጅ ሰይድ ኪያር ሁለት ተጫዋቾችን እና ግብ ጠባቂውን በማታለል አስቆጥሯል።የወላይታ ዲቻ ዋና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪ/ማሪያም እና ሰይድ ኪያር በጨዋታው ላይ ድንቅ እንቅስቃሴ በማድረጋቸው ከደጋፊዎች አድናቆት ተችሯቸዋል።

በጨዋታው የእረፍት ሰዓት የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ መርክነህ ማለደ ወጣቱን ተጫዋች ለመደገፍ ከአዲስ አበባ የመጡትን የጋዜጠኞች ቡድንን በማመስገን ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን በመቀጠል የከተማውን ነዋሪም አመስግነዋል።ክቡር ከንቲባውም በከተማ አስተዳደሩ ስም የመጀመሪያ ድጋፍ በሚል አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር(150,000) አበርክተው እስከመጨረሻው ድረስ ከይበልጣል ጎን እንደሚቆሙም ጭምር ገልፀዋል።

ከክቡር ከንቲባው በመቀጠል ፕሮግራሙን ያስተባበሩት የስፖርት ዞን አዘጋጆች ጋዜጠኛ ሰይድ ኪያርና መኳንንት በርሄ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ሰይድ ኪያር ይበልጣልን ማገዝ ሀገርን ማገዝ ነው ስለዚህ ሁላችንም ከጎኑ ልንቆም ይገባል እሱን ለማገዝ የተገኛችሁትን በሙሉ አመሰግናለሁ በማለት ንግግሩን ጨርሷል።

በቀጣይ ንግግር ያደረገው ጋዜጠኛ መኳንንት በርሄ ስፖርት ዞን የይበልጣልን ጉዳይ እንደራሳችን አድርገን እንድንይዘው ያደረግን ነገ ታዳጊዎች እሱን እያዩ እግር ኳስን እንዲጫወቱ እና እሱ የደረሰበት ደረጃ መድረስ እንደሚችሉም ለማሳየት ነው ብሏል።በመቀጠልም በስታዲየሙ የሃምሳ ብር የአንድ መቶ እና የሁለት መቶ ብር ኩፖን ህዝቡ እየገዛ ይበልጣልን እንዲያግዘው ጥሪ በማስተላለፍ በስፖርት ዞን ስም የአምሰት ሺህ ብር ኩፖን ገዝተዋል።ነገ ደግሞ የፕሪምየር ሊግ ተሳታፊዎቹ ወላይታ ዲቻ እና አርባ ምንጭ ከተማ ለይበልጣል ኤልያስ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ጨዋታ በዘጠኝ ሰዓት በወላይታ ሶዶ ስታዲየም ያደርጋሉ ።ህዝቡም አንድም በጨዋታው እየተዝናና አንድም ይበልጣልን እንዲደግፍ በክቡር ከንቲባ ጥሪ ቀርቦለታል።

ሀትሪክ ስፖርትም የይበልጣልን ጉዳይ እንደራሷ በማየት ቦታው ድረስ በመገኘት ሰፊ ሽፋን ሰታለች።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...