በኮስታሪካ አስተናጋጅነት በ2022 ለሚካሄደው የሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለ ገብርኤል ለ28 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ እስካሁን ያደረጋቸው ሦስት የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታዎች በአሸናፊነት የተወጣ ሲሆን በቀጣይ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ለሚያደርገው የአራተኛ የማጣርያ ዙር ጨዋታ ዛሬ ታህሳስ 30/2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ሀያት አካባቢ በሚገኘው የካፍ የልዕቀት ማዕከል የብሔራዊ ቡድን የስፖርት ትጥቃቸውን በመያዝ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች 28 ጫዋቾች የሚከተሉት ናቸው፦
ከአዲስ አበባ ከተማ፦ አርያት ኦዶንግ ፣ ማክዳ አሊ
ከአዳማ ከተማ፦ እየሩሳሌም ሎራቶ ፣ ናርዶስ ጌትነት
ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ ብዙአየሁ ታደሰ ፣ ትእግስት ሃይሌ ፣ አረጋሽ ካልሳ
ከድሬ ዳዋ ከተማ፡- ብርቄ አማረ ፣ ቤተልሔም ታምሩ ፣ ባንቺይርጋ ተስፋዬ
ከባህር ዳር ከተማ፡- ባንቺአየሁ ደመላሽ
ከኢትዮ ኤሌክትሪክ፡- ኝቦኝ የን ፣ መስከረም ኢሳያስ ፣ ገነት ኤርምያስ
ከመከላከያ ስፖርት ክለብ፡- መዓድን ሣህሉ ፣ ነፃነት ፀጋዬ ፣ ገነት ኃይሉ ፣ ቤተልሔም በቀለ ፣ እፀገነት ግርማ ፣ አይናለም አደራ ፣ መሳይ ተመስገን
ከሀዋሳ ከተማ፡- ቱሪስት ለማ ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ ፣ ቅድስት ቴቃ
ከቅዱስ ጊዮርጊስ፡- ንግስት አስረስ ፣ ሰናይት ሼጎ
ከቦሌ ክፍለ ከተማ፡- ንግስት በቀለ ፣ ንጋት ጌታቸው
አስተያየት ይስጡ