በፕሪሚየር ሊጉ ውጤታማ ጉዞ ያላደረጉት የፈረሰኞቹ ቦርድ ለመጨረሻ ውይይትና ለውሳኔ አሰልጣኙ ዝላትንኮ ክራንፓቲችን ወደ አዲስ አበባ ጠርቷል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ያለበትን ጨዋታ በምክትል አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታና ደረጄ ተስፋዬ የሚመራ መሆኑ ተረጋግጧል። ፕሪሚየር ሊጉ ከተጀመረ ወዲህ አሰልጣኝ ዘሪሁን ጊዮርጊስ ከሰበታ ከተማና ከድሬዳዋ ከተማ አቻ ሲለያይ እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡናን 4 ለ1 ሲረታ ቡድኑን መርቷል። ዝላታን ክራንፓቲች ደግሞ ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ከመከላከያና ከሲዳማ ቡና አቻ የተለያዩበትን ጨዋታ መርተዋል።
ውጤቱም የተለየ ለውጥ የሌለውና ለምን ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚከፈል በቀጣይም ውጤቱን ለመመለስ ምን መደረግ አለበት? አሰልጣኙስ ከሚጠበቅበት አንጻር ምኑን አሳካ ? በሚሉት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ለመወሰን ከአሰልጣኙ ጋር ሁለትዮሽ ውይይት ለማድረግ ለነገ ሰኞ ቀጠሮ መያዙ ታውቋል።
መረጃዎች ግን አሰልጣኙን ማሰናበት ከፍተኛ የካሳ ክፍያ ስለሚኖረው ውይይት አድርጎም በስምምነት ለመለያየት ሳይወሰን አይቀርም እያሉ ነው።
ፈረሰኞቹ አምስት ጨዋታ አድርገው አንዱን ረትተውና በአራቱ አቻ ተለያይተው ማግኘት ከነበረባቸው 15 ነጥቦች 7 ነጥብ ብቻ በማሳካት በሊጉ 8ኛ ደረጃ ይገኛሉ።
አስተያየት ይስጡ