መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የጨዋታ ዘገባ | የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችየጨዋታ ዘገባድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዘገባ | የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የድሬዳዋ ከተማ ጨዋታ በአቻ ውጤት ተጠናቋል

አጋራ
አጋራ

በሊጉ ሶስተኛ ሳምንት የመጨረሻ ዕለት ጨዋታዎች በቅድሚያ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ የተካሄደው የድሬዳዋ ከተማ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ተጠናቋል ።

በቋሚ አሰላለፍ በድሬዳዋ ከተማ በኩል ከሁለተኛው ሳምንት ጨዋታ ሶስት ያህል ቅያሪዎች የተደረጉ ሲሆን በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ደግሞ ሁለት ያህል ቅያሪዎች ተደርገዋል ።

በመጀመሪያው አጋማሽ በሁለቱም ክለቦች በኩል ረጃጅም ኳሶችን በመጠቀም የሚደረገለ ተደጋጋሚ ጥረቶች ተስተውለዋል ። ምንም እንኳን ተጋጣሚዎቹ በተደጋጋሚ የተቃራኒ ግብ ክልል እየተፈራረቁ መድረስ ቢችሉም የተሳኩ እና ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ ረገድ ደክመው ተስተውለዋል ። በአጋማሹ በድሬደዋ ከተማ በኩል ሊጠቀስ የሚችለው የግብ ሙከራ በ12ኛ ደቂቃ ላይ የተደረገ ሲሆን መሐመድ አብዱለጢፍ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካዮች ስህተት ያገኘውን ኳስ በሳጥን ውስጥ ሆኖ ቢሞክረውም ግብ ጠባቂው ቻርለስ ሉክዋጎ ሊመልሰው ችሏል ።

በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩልም ያን ያህል የድሬዳዋውን ግብ ጠባቂ ፍሬው ጌታሁንን የፈተኑ ሙከራዎች ማድረግ አልቻሉም ። ኳሶችን በረጅም እንዲሁም አልፎ አለፎ ከክንፍ በሚነሱ ወደ ግብ ለመድረስ ቢሞክሩም ከፊት መስመር ባለው አለመናበብ ምክንያት በተደጋጋሚ ይበላሽባቸው ነበር ። አቤል ያለው ፤ እስማኤል ኦጎሮ እንዲሁም በረከት ወልዴ በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ ግብ ኳሶችን ቢሞክሩም ኢላማቸውን ግን የጠበቁ አልነበሩም ።

የመጀመሪያ አጋማሽ መደበኛ ደቂቃ ተጠናቆ 4 ደቂቃዎች በተጨመሩበት ጊዜ ጨዋታው ከሁለቱም ክለቦች በኩል ግቦችን አገኘ ። በጨዋታው በተደጋጋሚ ኳሶች ይበላሹበት የነበረው አጥቂው እስማኤል ኦጎሮ በ45+2 ደቂቃ ላይ ከቀኝ መስመር በረጅሙ የተሻገረለትን ኳስ በመቆጣጠር እና የድሬዳዋ ከተማ ተከላካዮች በማታለል ፈረሰኞቹን መሪ ያደረገች ግብ አስቆጠረ ።

ቅዱስ ጊዮርጊሶች የመጀመሪያውን ጎል ደስታ አጣጥመው ሳይጨርሱ ድሬደዋ ከተማዎች በተመሳሳይ መልኩ ከረጅም የተነሳ ኳስ አስቆጠሩ ። ኳሱ ከግራ መስመር የተሻገረ ሲሆን የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካዮች መዘናጋትን ተጠቅሞ በፍጥነት ያለፈው ጋዲሳ መብራቴ ወደ ግብ ያሳለፈው ኳስ ግብ ጠባቂውን ሲያልፍ ማማዱ ሲዲቤ አግኝቶ ግብ አደረገው ። የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ በተጨማሪ ሰዓት በተቆጠሩት ግቦች 1 ለ 1 ተጠናቀቀ ።

በጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ ደጋፊዎች በኩል አንዲት ውሻ በድሬደዋ ከተማ ማልያ ቀለም አሸብርቃ ከደጋፊዎች ጋር ታይታለች ።

በሁለተኛው አጋማሽ በፈረሰኞቹ በኩል አማኑኤል ገብረ ሚካኤልን እና ጋቶች ፓኖምን በእስማኤል ኦጎሮ እና በረከት ወልዴ ቀይረው በማስገባት ጀምረዋል ። አሁንም በሁለቱም በኩል ረጃጅም ኳሶችን የመጠቀም ነገር ቢስተዋልም ቅዱስ ጊዮርጊሶች በፈጣን ተጫዋቾቻው አማካይነት ከክንፍ ተነስተው ወደ ሳጥን በመግባት የግብ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረቶችን ማድረግ ችለዋል ።

በድሬዳዋ ከተማ በኩል አልፎ አልፎ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሜዳ በመግባት ወደ ፊት ለመሄድ ያደርጉት የነበረው ጥረት ፈረሰኞቹ ተከላካዮች በቀላሉ ይበላሽባቸው ነበር ። ምናልባትም በጨዋታው የመጨረሻ ተጨማሪ ደቂቃዎች ላይ መሐመድ አብዱለጢፍ ከማዕዘን የመታው ኳስ በቀጥታ ግብ ሊሆን ሲል ሉክዋጎ ለጥቂት አውጥቶበታል ።

ጨዋታውም በአጋማሹ ተጨማሪ ሌላ ግብ ሳያስተናግድ የጨዋታውን መጠናቀቅ የሚያበስረው የመሀል ዳኛው ፊሽካ ድምፅ ተሰማ ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...