መነሻ ገጽ ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የጨዋታ ዘገባ | አርባምንጭ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን በአንድ እኩል ውጤት አጠናቀዋል
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአርባምንጭ ከተማዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | አርባምንጭ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ጨዋታቸውን በአንድ እኩል ውጤት አጠናቀዋል

አጋራ
አጋራ

በዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ የተገናኙት አርባምንጭ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና ያደረጉትን ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት አጠናቀዋል ።

በጨዋታው ቋሚ አሰላለፍ ላይ በሁለቱም በኩል ከሁለተኛው ሳምንት ጨዋታቸው ቅያሪዎች የነበሩ ሲሆን በአርባምንጭ ከተማ በኩል አራት እንዲሁም በሀድያ ሆሳዕና በኩል ሁለት ቅያሪዎችን በማድረግ ወደ ጨዋታው ገብተዋል ።

የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ተመጣጣኝ እንቅስቃሴን ያስመለከተ ነበር ። በሁለቱም ክለቦች በኩል ወደ ግብ በመቅረብ በተጋጣሚ ላይ ግብ ለማስቆጠር በተለያዩ አጋጣሚዎች ጥረቶች ቢደረጉም የተሳኩ የግብ ሙከራዎችን ማድረግ ግን ተስኗቸዋል ። በ11ኛው ደቂቃ ላይ በአርባ ምንጭ ከተማ በኩል ሀቢብ ከማል ከሳጥን ውጪ ያደረገው ምርጥ ሙከራ በግብ ጠባቂው ሜንሳህ ተይዞበታል ።

በጨዋታው 13ኛ ደቂቃ ላይ የሀድያ ሆሳዕናው አምበል ሄኖክ አርፊቾ ባጋጠመው ጉዳት በእያሱ ታምሩ ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል ። በ18ኛው ደቂቃ ላይ ግልፅ የማግባት ዕድል ያገኙት አርባ ምንጭ ከተማዎች ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል ኤሪክ ካፓይቶ ከተከላካዩ በርናንድ ኦቼንግ ጥሩ ኳስ ደርሶት ከግብ ጠባቂው ፊት ለፊት ቢገናኝም ጠንከር አድርጎ ባለመምታቱ ሜሱ የመለሰበት ሲሆን የተመለሰውን ኳስም ያገኘው ፀጋዬ አበራ ወደ ግብ ቢመታውም ኳሱ ኢላማውን ሳይጠብቅ ቀርቷል ። በሀድያ ሆሳዕና በኩል በመጀመሪያው አጋማሽ ያደረጉት ተጠቃሽ ሙከራ 24ኛ ደቂቃ በኡመድ ኡክሪ ቢያደርጉም ወደ ውጪ ወቷል ።
በቀጣይ ደቂቃዎች በብዛት ኳሶች በመሀል ሜዳው ላይ የቆዩ ሲሆን የመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽም ያለምንም ግብ ተጠናቀቀ ።

የሁለተኛው አጋማሽ ከተጀመረ ከአራት ደቂቃ በኋላ አርባምንጭ ከተማ በበላይ ገዛኸኝ አማካኝነት የመጀመሪያ ግብ አስቆጠሩ ። ኳሱ ከፀጋዬ አበራ ከግራ መስመር ተሻምቶ ግብ ጠባቂው ሜሱ መያዝ ሳይችል ቀርቶ አጠገቡ የነበረው በላይ መቶ ሊያስቆጥረው ችሏል ። ከግቡ መቆጠር በኋላ ሀድያ ሆሳዕና ቀደም ብሎ ከነበረው በተሻለ ወደ ፊት በመሄድ ጫና ለመፍጠር ጥረቶችን ማድረግ ችለዋል ።

በዚህም በ59ኛ ደቂቃ ላይ የአቻነቷን ግብ ማግኘት ችለዋል ። ከቀኝ መስመር ላይ ብርሀኑ በቀለ ያሻገረው ኳስ በአርባምንጭ ከተማ ተከላካዮች ሲመለስ ፈጥኖ የደረሰው ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ወደ ግብ መቶ አስቆጠረው ። ከግቧ በኋላም ሀድያ ሆሳዕናዎች ከአርባምንጭ ከተማ በተሻለ ወደ ግብ መድረስ የቻሉ ሲሆን በተለይም ባዬ ገዛኸኝ ሁለት ያለቀላቸው ኳሶችን አስቆጠራቸው ተብሎ ሲጠበቀው ወደ ውጪ መቷቸዋል ።

በአርባምንጭ ከተማ በኩል በአጋማሹ ወደ ተጋጣሚ ግብ ክልል በመድረስ ረገድ ደክመው ተስተውለዋል ። በጨዋታው 84ኛ ደቂቃ ላይም የሀድያ ሆሳዕና ግብ አስቆጣሪ ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል። ጨዋታውሞ በሁለቱ ግቦች ብቻ ተወስኖ 1 ለ 1 ተጠናቀቀ ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...