መነሻ ገጽ ሀዋሳ ከተማ የጨዋታ ዘገባ | የጦና ንቦቹ በሀብታሙ ንጉሴ ብቸኛ ግብ ድል ቀንቷቸዋል
ሀዋሳ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግወላይታ ድቻዜናዎችየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | የጦና ንቦቹ በሀብታሙ ንጉሴ ብቸኛ ግብ ድል ቀንቷቸዋል

አጋራ
አጋራ

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሁለተኛ ሳምንት ሁለተኛ ጨዋታ ልክ እንደመጀመሪያው ጨዋታ ሁሉ በ 1 ለ 0 ውጤት ተጠናቋል ።

በመጀመሪያ ጨዋታቸው ተቃራኒ ውጤትን ያስመዘገቡ ሲሆን ሀዋሳ ከተማ ጅማ አባጅፋርን አሸንፎ እንዲሁም ወላይታ ድቻ በድሬዳዋ ከተማ ተሸንፎ ነበር ።

ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጅማሬውን ያደረገ ሲሆን በወላይታ ድቻ በኩል ከመጀመሪያው የሊጉ ጨዋታቸው አንድ በሀዋሳ ከተማ በኩል ደግሞ ሶስት ቅያሪዎች በማድረግ ነበር የዕለቱን ጨዋታ ለማድረግ ወደ ሜዳ የገቡት።

በጨዋታው በሀዋሳ ከተማ በኩል የኳስ ቁጥጥር ብልጫ በመውሰድ ግብ ለማስቆጠር የጣሩ ሲሆን በአንፃሩ በወላይታ ድቻ በኩል የሚገኙ ኳሶችን በፍጥነት ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል በመውሰድ ግብ ለማድረግ ሞክረዋል ።

በጨዋታው 11ኛ ደቂቃ ላይ በሀዋሳ ከተማ በኩል ኤፍሬም አሻሞ ከግራ መስመር የተሻገረለትን ኳስ በአጨራረስ ችግር ሳይጠቀምበት ቀርቷል ። 25ኛ ደቂቃ ላይ የጨዋታው የመጀመሪያ ግብ ተቆጠረ ። የወላይታ ድቻው አጥቂ ስንታየሁ መንግስቱ በፈጣን እንቅስቃሴ ያገኘውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮት በግብ ጠባቂው ዳግም ተፈራ ቢመለስም የተመለሰውን ኳስ ያገኘው ሀብታሙ ንጉሴ ኳሱን ከመረብ ማሳረፍ ቻለ ። ወላይታ ድቻ 1 – 0 ሀዋሳ ከተማ

ከግቧ መቆጠር በኋላ የአቻነቷን ግብ ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ወላይታ ድቻ ያመሩት ሀዋሳ ከተማዎች በ34ኛው በ38ኛ ደቂቃ ላይ በብሩክ በየነ አማካኝነት ጥሩ ሙከራዎችን ማድረግ ችለው የነበረ ሲሆን በመሪዎቹ በወላይታ ድቻ በኩል የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ደቂቃዎች ላይ በምንይሉ ወንድሙ አማካኝነት መሪነታቸውን ማስፋት የሚችሉበትን ዕድል ቢያገኙም ሳይጠቀሙበት ቀርተው የመጀመሪያው አጋማሽ 1 ለ 0 በሆኘ ውጤት ተጠናቀቀ ።

በሁለተኛው አጋማሽ ሀዋሳ ከተማዎች በከፍተኛ በማጥቃት ግብ ለማስቆጠር ጥረቶችን ቢያደርጉም ፍሬያማ ግን አልነበሩም ። በተለይም በብሩክ ኤሊያስ ፤ በመስፍን ታፈሰ እና በብሩክ በየነ አማካኝነት የግብ ሙከራዎችን ቢያደርጉም ጎል ማግኘት ግን አልቻሉም ። በአንፃሩ በወላይታ ድቻ በኩል ወደኋላ አፈግፍገው በመጫወት በጠንካራ መከላከል ተጋጣሚያቸውን ግብ እንዳያስቆጥርባቸው ያደረጉ ሲሆን ኳሶች በእግራቸው ስር ሲገቡ ደግሞ በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማስቆጠር ጥረቶችን አድርገዋል ።

ጨዋታው በዚህ ሁኔታ ቀጥሎ ከሀብታሙ ንጉሴ ግብ ውጪ ተጨማሪ ሌላ ግብ ሳያስተናግድ የዕለቱ የመሀል ዳኛ የጨዋታ ማጠናቀቂያ ፊሽካ ድምፅ ተሰማ ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...