መነሻ ገጽ ሉሲዎቹ “ሩዋንዳ ላይ አሰልጣኝ ፍሬው ጎል እንደማስቆጥር ደጋግሞ ይነግረኝ ነበር”ረድኤት አስረሳኸኝ
ሉሲዎቹዜናዎች

“ሩዋንዳ ላይ አሰልጣኝ ፍሬው ጎል እንደማስቆጥር ደጋግሞ ይነግረኝ ነበር”ረድኤት አስረሳኸኝ

አጋራ
አጋራ

“በልጅነቴ ሎዛ አበራን እያየሁ ነው ያደኩት”

“ሩዋንዳ ላይ አሰልጣኝ ፍሬው ጎል እንደማስቆጥር ደጋግሞ ይነግረኝ ነበር”

ከ20 አመት በታች የሴቶች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአለም ዋንጫ ማጣሪያውን እያደረገ ይገኛል ።በማጣሪያ ጨዋታዎች ለሀገሯ አራት ጎሎችን ካስቆጠረችው እና በየጨዋታዎቹ ድንቅ አቋሟን እያሳየች ካለቸው ረድኤት አስረሳኸኝ ጋር ስለ አለም ዋንጫው ማጣሪያ ከሀትሪክ ስፖርት ሪፖርተር እና ፎቶግራፈር AKU ጋር ቆይታ አድርጋለች

 

በመጀመሪያ ሩዋንዳ ላይ ባገኛችሁት ውጤት እንኳን ደስ አላችሁ ብዬ ልጀምር

ረድኤት:- እንኳን አብሮ ደስ አለን

ወደ ሩዋንዳ ከመሄዳቹ በፊት ለጨዋታው ምን ያህል ዝግጅት አድርጋችሁ ነበር?

ረድኤት:-የመጀመሪያ ዙር ጨዋታችን ከሜዳችን ውጪ ስለነበር ቀደም ብለን ነው ዝግጅት የጀመርነው: ለጨዋታው 25 ቀናቶች ሲቀሩን ወደ ዝግጅት ገባን አስሩን ቀን በቀን ሁለት ጊዜ ጠንከር ያሉ ልምምዶችን ሰራን የቀሩትን ቀናቶች በቀን አንድ ጊዜ ከኳስ ጋር በተገናኘ ስንሰራ ነበር።

በልምምድ ወቅት የነበራችሁ ተነሳሽነት እንዴት ነበር?

ረድኤት:-ሁሉም ጋር የነበረው መንፈስ ደስ ይል ነበር ልምምዳችንንም በፍላጎት ነበር የምንሰራው በዚህም አሰልጣኛችን በጣም ደስተኛ ነበር።

ወደ ሩዋንዳ ጉዞ ካደረጋችሁ በኋላ ዝግጅታችሁ ምን ይመስል ነበር?

ረድኤት:- ሩዋንዳ ላይ የተለየ ልምምድ አልሰራንም ነገር ግን አሰልጣኛችን በሚሰጠን ልምምድ ደስተኛ ሆነን በወኔ እና በፍላጎት እንሰራ ነበር ።ሁልጊዜም ከልምምድ በኋላ አሰልጣኛችን የክላስ ትምህርቶችን ይሰጠናል ስለ ጨዋታው በሚያወራ ጊዜ ጨዋታውን ከእረፍት በፊት መጨረስ እንዳለብን በተደጋጋሚ ጊዜ ይነግረናል :በጨዋታውም እሱ ያዘዘንን ስላደረግን ነው ውጤታማም የሆነው።

እስቲ ወደ አንቺ እንምጣና ጨዋታው እንዴት ነበር ለአንቺ?

ረድኤት:-ወደ ሜዳ ከመግባቴ በፊት አሰልጣኜ የሚለኝን ነገር ለማድረግ እያሰብኩ እና እሱ ያለኝን ካደረኩ እንደሚቀለኝ አስብ ነበር : እግዚአብሔርም ረድቶኝ የአሰልጣኜን ትዕዛዝ ተቀብዬ ወደ ሜዳ ገባው እንዳያችሁት በግሌም ሁለት ጎሎችን አስቆጥሬ ውጤታማ ሆኜ ወጣው :ለዚህም አሰልጣኝ ፍሬውን በጣም አመሰግናለሁ

ጎሎቹን ካስቆጠርሽ በኋላ ሰለነበረሽ ደስታ አገላለጽ ?

ረድኤት:- እውነት ነው በጣም ደስተኛ ነበርኩ የመጀመሪያ ምክንያቴ ለሀገሬ ያለኝ ፍቅር ነው ሁለተኛው ደግሞ እዚህ ደረጃ ለመድረስ በጣም ለፍቻለው እና የለፋውበትን ውጤት ስላገኘው ነው ።

ሩዋንዳ ላይ ኮከብ ነበርሽ አሰልጣኝሽ በአንቺ ላይ ያሳረፈው አሻራ ይኖር ይሆን?

ረድኤት:- በሚገባ ነዋ ያሳረፈው እዚህ ደረጃ እንድደርስ ካገዙኝ ሰዎች አንደኛው እሱ ነው በእሱ ምክንያት ነው ኮከብ የሆንኩት ጨዋታ ከመግባታችንም በፊት ጎሎችን እንደማስቆጥር ደጋግሞ ይነግረኝ ነበር : ለዛም ነው ሁለት ጎሎችን ያስቆጠርኩት።

ከሜዳችን ውጪ ትልቅ ውጤት ነው ያስመዘገብነው የሌላ ሀገር ተጨዋቾች ከእኛ የተለየ ነገር ምን አላቸው ብለሽ ታስቢያለሽ?

ረድኤት:- በእኔ በኩል ምንም የተለየ ነገር አላየሁባቸውም : ምን አልባት እነሱ ጋር ለሴቶች እግር ኳስ የሚሰጠው ትኩረት ሀገራችን ላይ ቢኖር አሁን እያስመዘገብነው ካለው ውጤት በላይ እናስመዘግባለን ብዬ አስባለው : ይሄን ስል ሀገራችን ውስጥ ለሴቶች እግር ኳስ ትኩረት አልተሰጠም ሳይሆን ታች ድረስ ትኩረት ተሰጥቶ ከተሰራ ከእነሱ የተሻለ አቅም ስላለን ከዚህ የተሻለ ውጤት እናስመዘግባለን ብዬ አስባለው።

ስለ ነገው ጨዋታ ምን ታስቢያለሽ?

ረድኤት:-እንግዲህ ነገ ከእግዚአብሔር ጋር እናሸንፋለን በዚህም እርግጠኛ ነኝ :ከእኛ የሚጠበቀው አሰልጣኛችን የሚያዘንን ሜዳ ውስጥ መተግበር ብቻ ነው እሱ ያለንን ከተገበርን ውጤታማ የማንሆንበት ምክንያት አይታየኝም በዛ ላይ ጨዋታችንን የምናደርግበት የባህር ዳር ስታዲየም አንድም ሽንፈት አስተናግዶ ስለማያውቅ ይሄንንም ሪከርድ ለማስጠበቅ እንጫወታለን።

ለነገው ጨዋታ የተለየ ያደረግሺው ነገር አለ ?ከአንቺስ ጎል እንጠብቅ?

ረድኤት:-ምንም የለም ልምምዴን በሚገባ ሰርቻለው ለጨዋታውም በቂ እረፍት እያደረኩ እገኛለው።ነገ ጎል አስቆጥራለው ብዬ አስባለው እግዚአብሔርም ይረዳኛል

ስለ እግር ኳስ ህይወቷ?

ረድኤት:-እግር ኳስን መጫወት የጀመርኩት ሎዛ አበራን እያየሁ ነው የዱራሜ ልጅ እንደመሆናችን ሁልጊዜም እሷ የምትሰራቸውን ልምምዶች እሰራ ነበር ከዛ በተረፈ አብዛኛውን ጊዜ ለብቻዬ ልምምዶችን በደንብ እሰራለው እረፍት አደርጋለው : ወደ ክለብ ከተቀላቀልኩ በኋላም የተቀየረ ነገር አልነበረም ከአሰልጣኞቼ የሚሰጡኝን ልምምዶች በሚገባ እየሰራው እረፍት አደርጋለው ።

ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ የማን አድናቂ ነሽ ከእግር ኳስ ተጨዋቾች?

ረድኤት:- ከሀገር ውስጥ ቀድሜ እንደነገርኩህ የሎዛ አበራ አድናቂ ነኝ የምታገባቸው ጎሎች ለጓደኞቿ አመቻችታ የምታቀብልበት መንገድ እና ራስ ወዳድ አለመሆኗ ሁሌም እንዳከብራት እና እንዳደንቃት አድርጎኛል ።ከሀገር ውጪ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አድናቂ ነኝ ታታሪነቱን አልሸነፍ ባይነቱን እና ዳኛው የመጨረሻ ፊሽካ እስከሚነፋ ድረስ ተስፋ አለመቁረጡ እንዳደንቀው አድርጎኛል።

ትርፍ ጊዜሽን በምንድነው የምታሳልፊው?

ረድኤት:-በትርፍ ጊዜዬ ቤተክርስቲያን እሄዳለው መፅሐፍ ቅዱስ አነባለው አንዳንዴ ከጓደኞቼ ጋር ወክ እናደርጋለን ጨዋታ ካለም አያለው ።

በመጨረሻ ማመስገን የምትፈልጊው

ረድኤት:- በመጀመሪያ እዚህ እንድደርስ ምህረቱን እና ቸርነቱን ላበዛልኝ ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው ።በመቀጠል ከልጅነት ጀምሮ ኳስን እንድጫወት ሲያግዘኝ እና ሲያበረታታኝ ለነበረው ለአሁን የከምባታ ሴቶች ቡድን አሰልጣኝ አስራት ዮሐንስ እና አድማሱ ደቦጭ እንዲሁም የዲላው አሰልጣኝ እንዳልክ የሀዋሳ ከነማው አሰልጣኝ መልካሙ ታፈረን ከልብ አመሰግናለሁ ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገሬን እንዳገለግል ከ17 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን እንድቀላቀል ጥሪ ያደረገችልኝ ኢንስትራክተር ሰላም ዘርአይን ከልብ አመሰግናለሁ በመጨረሻ አሁን ላለሁበት ደረጃ እንድደርስ እያገዘኝ የሚገኘው አሰልጣኝ ፍሬው ሀ/ገብርኤልን እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ።እናንተም አክብራችሁ እንግዳችሁ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...