የታችኞቹ ሊግስ..?
የከፍተኛ ሊግና የአንደኛ ሊግ የደመወዝ ገደብ አለመነሳቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ካምፓኒ ከክለቦች ጋር በመነጋገር የነበረውን የ50 ሺህ ብር ገደብ በማንሳት ዝውውሩ ነጻ እንዲሆን ማድረጉ ይታወቃል።
የመድን እግር ኳስ ክለብ ተጨዋቾቹን በ25ሺህ ብር ለማስፈረም ያደረገው ጥረት የከሸፈ ሲሆን በተቀመጠው ህግ መሠረት ገደቡ 20 ሺህ ብር መከበር እንዳለበት ከፌዴሬሽኑ ተነግሮታል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን “ህጉ የወጣው በሶስቱ ሊጎች ክለቦች አማካይነት ነው ፕሪሚየር ሊጉን ተካፋይ ክለቦቹ ገደቡን አንስተው ፌዴሬሽኑም
ተቀብሎታል የከፍተኛ ሊግና የአንደኛ ሊግ ክለቦችም ገደቡን ማንሳት መብታቸው ነው እስካላነሱ ድረስ ግን የከፍተኛ ሊግ 20 ሺህብር አንደኛ ሊጉ 5ሺህ ብር ገደቡን መጣስ አይቻልም” ሲል አስታውቋል። ይሄ ገደብ ካልተነሳ በሊጎቹ ባሉ ተጨዋቾች ላይ ከፍተኛ የሞራል ኪሳራ ሊያመጣ ይችላልጰተብሎ ተሰግቷል።
በተፈጠረው ልዩነት ዙሪያ የተጠየቀው የፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾችና ባለሙያዎች ማህበር በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት መረጃ እንደሌለውና ከሁለቱ ሊጎች ተጨዋቾች የደረሰው ቅሬታ እንደሌለ አስታውቋል።
አስተያየት ይስጡ