…ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ምርጥ ዜና…
ከአመታት በፊት በወቅቱ በነበሩ የክለቡ ፕሬዝዳንት የጥቂት ደቂቃ ጋዜጣዊ መግለጫ የፈረሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእግር ኳስ ቡድን ዳግም ነፍስ ሊዘራ መሆኑ ተሰምቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኔ የዋና ቡድን ከ17 እና 20 አመት በታች ቡድኖች እንዲመሠረቱ በሰጡት መመርያ መሠረት የሶስቱ ቡድኖች የአሰልጣኝ ቅጥር ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ ዛሬ የወጣ ሲሆን ከነገ ጀምሮ ባሉት10 የስራ ቀናት ላይ አሰልጣኞች መወዳደር እንደሚችሉ ተገልጿል። ይሄ የፕሬዝዳንቱ ውሳኔ በደቂቃ መግለጫ በፈረሰው ታሪካዊው ንግድ ባንክ መፍረስ ላረሩት የስፖርት ቤተሰቦች ምርጥ የአዲስ አመት ስጦታ ይመስላል።
የክለቡ አመራሮች እንደባለፈው ሳይሆን ለአሰልጣኞቹ መብትና የስራ ነጻነት ሰጥቶ ነገር ግን ቁጥጥር የሚያደርግ አሰልጣኞቹን የሚያግዙ የቦርድ አባላት ሊያዋቀሩለት እንደሚገባ ይታመናል።
አስተያየት ይስጡ